Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 24:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አማሌቅንም አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ አማሌቅ የአሕዛብ አለቃ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት ይመጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚያም በለዓም አማሌቅን አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “አማሌቅ ከሕዝቦች የመጀመሪያው ነበር፤ በመጨረሻ ግን ይደመሰሳል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በለዓምም አማሌቅን አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የአሕዛብ መጀመሪያ የሆነ አማሌቅ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት የሚያመራ ይሆናል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከዚህ በኋላ በለዓም ወደ ዐማሌቅ በመመልከት እንዲህ ሲል ይህን የትንቢት ቃል ተናገረ፦ “ዐማሌቅ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል ሕዝብ ነበረ፤ በመጨረሻ ግን እርሱ ራሱ ለዘለዓለም ይጠፋል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ዐማ​ሌ​ቅ​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ዐማ​ሌቅ የአ​ሕ​ዝብ አለቃ ነበረ፤ ዘራ​ቸ​ውም ይጠ​ፋል።”

参见章节 复制




ዘኍል 24:20
18 交叉引用  

ቲምናዕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ የጭን ገረስ ነበረች፥ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጆች እነዚህ ናቸው።


ያመለጡትንም የአማሌቃውያንን ቅሬታ መቱ፤ በዚያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጠዋል።


ከዚህም ነገር በኋላ ንጉሡ አርጤክስስ የአጋጋዊውን የሐመዳቱን ልጅ ሐማን ከፍ ከፍ አደረገው፥ አከበረውም፥ ወንበሩንም ከእርሱ ጋር ከነበሩት አዛውንት ሁሉ በላይ አደረገለት።


ንጉሡም ይህ ይደረግ ዘንድ አዘዘ፥ አዋጅም በሱሳ ተነገረ፥ አሥሩንም የሐማን ልጆች ሰቀሉ።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥


እርሱም፦ እጁን በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ስለጫነ የእግዚአብሔር ሰልፍ በአማሌቅ ላይ ለልጅ ልጅ ይሁን አለ።


አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ።


ከያዕቆብም የሚወጣ ገዥ ይሆናል፥ ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል።


ከኪቲም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፥ አሦርንም ያስጨንቃሉ፥ ዔቦርንም ያስጨንቃሉ፤ እርሱም ደግሞ ወደ ጥፋት ይመጣል።


ከማድጋዎቹ ውኃ ይፈስሳል፥ ዘሩም በብዙ ውኆች ይሆናል፥ ንጉሡም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፥ መንግሥቱም ይከበራል።


እስራኤልም ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያን አማሌቃውያንም በምሥራቅም የሚኖሩ ሰዎች ይመጡባቸው ነበር፥


እርሱም ጀግና ነበረ፥ አማሌቃውያንንም መታ፥ እስራኤልንም ከዘራፊዎቹ እጅ አዳነ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ።


እንዲህም ሆነ፥ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ በመጡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በደቡብ አገርና በጺቅላግ ላይ ዘምተው ነበር፥ ጺቅላግንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፥


ዳዊትም ከማታ ጀምሮ እስከ ማግሥቱ ማታ ድረስ መታቸው፥ ከእነርሱም በግመል ተቀምጠው ከሸሹ ከአራት መቶ ጕልማሶች በቀር አንድ ያመለጠ የለም።


跟着我们:

广告


广告