Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 24:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል፥ የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “አየዋለሁ፤ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፤ በቅርቡ ግን አይደለም፤ ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፤ በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይነሣል። የሞዓብን ግንባሮች፣ የሤትንም ወንዶች ልጆች ራስ ቅል ያደቅቃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤልም በትረ መንግሥት ይነሣል፥ የሞዓብንም ግንባር ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 አየዋለሁ፤ ነገር ግን አሁን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፤ ግን በቅርብ አይደለም፤ ኮከብ ከያዕቆብ፥ በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይወጣል። የሞአብን ድንበር፥ የሴትንም ዘሮች ሁሉ ይደመስሳል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤ ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤ የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።

参见章节 复制




ዘኍል 24:17
33 交叉引用  

በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።


በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮች አኖረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ እግዚአብሔርም ዳዊት በሚሄድበት ሁሉ ድልን ሰጠው።


ሞዓብን መታ፥ ሞዓባውያንንም በምድር ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፥ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ሙሉ ለሕይወት ሰፈራቸው፥ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት።


አክዓብም ከሞተ በኋላ የሞዓብ ንጉሥ በእስራኤል ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


ሞዓብን መታ፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።


ስለ ሞዓብ የተነገረ ሸክም። የሞዓብ ኤር በሌሊት ፈርሶ ጠፋ፥ ቂር የሚባልም የሞዓብ ምሽግ በሌሊት ፈርሶ ጠፋ።


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።


ስለ ሞዓብ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች ተይዛማለች፥ ሚሥጋብ አፍራለች ደንግጣማለች።


የሸሹ ደክመው ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፥ እሳት ከሐሴቦን ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአል የሞዓብንም ማዕዘን የሤትንም ልጆች አናት በልቶአል።


ከእርሱ ዘንድ የማዕዘኑ ድንጋይ፥ ከእርሱም ዘንድ ችንካሩ፥ ከእርሱም ዘንድ የሰልፍ ቀስት፥ ከእርሱም ዘንድ አስገባሪው ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ።


በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፥ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፥ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የከሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፥ ሴቶች ልጆቹንም ለምርኮ፥ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ።


የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ የልዑልንም እውቀት የሚያውቅ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ የወደቀው፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦


ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፤


ይላል፤ ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።


ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ ነውና፥ ስለዚህም ነገድ ሙሴ ምንም እንኳ ስለ ክህነት አልተናገረም።


ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።


ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።


እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።


ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል


እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።


ሳኦልም፦ እናንተ የሕዝቡ አለቆች ሁሉ፥ ወደዚህ ቅረቡ፥ ዛሬ ይህ ኃጢአት በምን እንደ ሆነ እወቁ፥ ተመልከቱም፥ እስራኤልን የሚያድን ሕያው እግዚአብሔርን! ኃጢአቱ በልጄ በዮናታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞታል አለ። ከሕዝቡም ሁሉ አንድ የመለሰለት ሰው አልነበረም።


跟着我们:

广告


广告