Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 23:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ይዋሽ ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፤ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፤ ተናግሮ አያደርገውምን? ተስፋ ሰጥቶስ አይፈጽመውምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እግዚአብሔር እንደ ሰው አይዋሽም፤ ሐሳቡንም እንደ ሰው አይለውጥም የሰጠውን ተስፋ ሁሉ ይፈጽማል፤ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰው የሚ​ታ​ለል አይ​ደ​ለም። እንደ ሰው ልጅም የሚ​ዛ​ት​በት አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ያለ​ውን አያ​ደ​ር​ገ​ው​ምን? አይ​ና​ገ​ረ​ው​ምን? አይ​ፈ​ጽ​መ​ው​ምን?

参见章节 复制




ዘኍል 23:19
36 交叉引用  

በዚህች ምድር ተቀመጥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።


እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በምትሄድባትም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድርስ አልተውህምና።


ከኢዮርብዓምም ወገን በከተማይቱ ውስጥ የሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳውም የሞተውን የሰማይ ወፎች ይበሉታል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።’


ለኢዩ “ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ፤” ተብሎ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነበረ፤ እንዲሁም ሆነ።


ንጉሡም በእጁ ተደግፎ የነበረ አለቃ ለእግዚአብሔር ሰው መልሶ “እነሆ፥ እግዚአብሔር በሰማይ መስኮቶች ቢያደርግ ይህ ነገር ይሆናልን?” አለው። እርሱም “እነሆ፥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፤ ከዚያም አትቀምስም፤” አለ።


አምላክ ሆይ! ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ስለ ባሪያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ።


ከቀስተኞች ቍጥር የቀሩት፥ የቄዳር ልጆች ኃያላን፥ ያንሳሉ፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።


እርሱ ግን ደግሞ ጠቢብ ነው፥ ክፉንም ነገር ያመጣል፥ ቃሉንም አይመልስም፥ በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።


ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ ያምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።


ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን፥ ከሩቅም አገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራለሁ። ተናግሬአለሁ እፈጽምማለሁ፥ አስቤአለሁ አደርግማለሁ።


ከአፌ የሚወጣ ቃል እንዲሁ ይሆናል፥ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።


ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠቍራል፥ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፥ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም።


ይህ ሁሉ በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ደረሰ።


እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ በመካከልህም ቅዱሱ ነኝና የቁጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፥ ኤፍሬምንም አጠፋ ዘንድ አልመለስም፥ በመዓትም አልመጣም።


ከቀድሞ ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን የማልህላቸውን እውነት ለያዕቆብ፥ ምሕረትንም ለአብርሃም ታደርጋለህ።


ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፥ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፥ እርሱ አይዘገይም።


እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፥ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።


እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።


ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ ባላቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ ስማ፤ የሴፎር ልጅ ሆይ፥ አድምጠኝ፤


ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።


እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።


ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም፥


ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ወይስ መጽሐፍ፦ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?


እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።


የእስራኤል ኃይል እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይዋሽም አይጸጸትምም አለው።


በዚያም ቀን በቤቱ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ በዔሊ አወርዳለሁ፥ እኔም ጀምሬ እፈጽምበታለሁ።


跟着我们:

广告


广告