Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 22:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሞዓብም የምድያምን ሽማግሌዎች፦ በሬ የለመለመውን ሣር እንደሚጨርስ ይህ ጭፍራ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ይጨርሳል አላቸው። በዚያን ጊዜም የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሞዓባውያንም የምድያምን ሽማግሌዎች፣ “በሬ የመስክ ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ፣ ይህም ሰራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሏቸው። ስለዚህ በዚያ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሞዓብም የምድያምን ሽማግሌዎች፦ “በሬ የለመለመውን የሣር መስክ ግጦ እንደሚጨርስ ይህ ጭፍራ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ አሁን ይጨርሳል” አላቸው። በዚያን ጊዜም የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሞአባውያን ለምድያማውያን ሽማግሌዎች “ይህ የምታዩት የሕዝብ ብዛት በሬ በመስክ የሚገኘውን ሣር ሁሉ ጠራርጎ እንደሚበላ በዙሪያችን ያለውን ነገር ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሉአቸው። ስለዚህ በዚያን ጊዜ የሞአብ ንጉሥ የነበረው የጺጶር ልጅ ባላቅ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሞዓ​ብም የም​ድ​ያ​ምን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “በሬ የለ​መ​ለ​መ​ውን ሣር እን​ደ​ሚ​ጨ​ርስ ይህ ሠራ​ዊት በዙ​ሪ​ያ​ችን ያለ​ውን ሁሉ ይጨ​ር​ሳል” አላ​ቸው። በዚ​ያን ጊዜ የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ የሞ​ዓብ ንጉሥ ነበረ።

参见章节 复制




ዘኍል 22:4
13 交叉引用  

ከምድያምም ተነሥተው ወደ ፋራን መጡ፤ ከእነርሱም ጋር ከፋራን ሰዎች ወሰዱ፤ ወደ ግብጽም መጡ፤ ወደ ግብጽም ንጉሥ ወደ ፈርዖን ዘንድ ገቡ፤ እርሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረገው፤ ምድርም ሰጠው።


የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞአብን ኃያላን መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።


ሞዓብን እንደማይወደድ ዕቃ ሰብሬአለሁና በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ በአደባባዩም ላይ በሁሉም ቦታ ልቅሶ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር።


የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞራውያን ላየ ያደረገውን ሁሉ አየ።


የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የምዋርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃል ነገሩት።


አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል፥ የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል።


እነሆም፥ ከእስራኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙሴና በእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ፊት ምድያማዊቱን አንዲቱን ሴት ወደ ወንድሞቹ አመጣት፤ እነርሱም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያለቅሱ ነበር።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት።


ወይስ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ አንተ ትሻላለህን? በውኑ እርሱ እስራኤልን ከቶ ተጣላውን? ወይስ ተዋጋውን?


የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፥ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።


跟着我们:

广告


广告