ዘኍል 21:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ስለዚህ ሙሴ የናስ እባብ ሠርቶ በዕንጨት ላይ ሰቀለ፤ ከዚያም በእባብ የተነደፈ ማንኛውም ሰው ወደ ናሱ እባብ በተመለከተ ጊዜ ይድን ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በእንጨት ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ሙሴም የነሐስ እባብ ሠርቶ በእንጨት ላይ ሰቀለው፤ በእባብ የተነከሰም ሁሉ ወደ ነሐሱ እባብ ቀና ብሎ ሲመለከት ዳነ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። 参见章节 |