Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 21:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከሖርም ተራራ ከኤዶምያስ ምድር ርቀው ሊዞሩ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ የሕዝቡም ሰውነት ከመንገዱ የተነሣ ደከመ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እስራኤላውያን በኤዶም ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ በመንገድ ሳለ ትዕግሥቱ ዐለቀ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከሖርም ተራራ የኤዶምያስን ምድር በዙርያው አድርገው ለመሄድ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ ሕዝቡም በመንገድ እየተጓዙ ሳሉ ጉልበታቸው ደከመ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እስራኤላውያን በኤዶም ግዛት ዙሪያ ለመሄድ አስበው ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ነገር ግን በመንገድ ሳሉ የሕዝቡ ትዕግሥት አለቀ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከሖ​ርም ተራራ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ተጓዙ፤ የኤ​ዶ​ም​ንም ምድር ዞሩ​አት፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ገድ ተበ​ሳጩ።

参见章节 复制




ዘኍል 21:4
14 交叉引用  

ደግሞም “በምን መንገድ እንሄዳለን?” አለ፤ እርሱም “በኤዶምያስ ምድረ በዳ መንገድ፤” ብሎ መለሰ።


ሙሴም ይህን ለእስራኤል ልጆች ተናገረ፤ እነርሱ ግን ከሰውነታቸው መጨነቅ ከከባዱም ሥራ የተነሣ ቃሉን አልሰሙትም።


አማሌቅና ከነዓናዊውም በሸለቆው ውስጥ ተቀምጦአል፤ በነጋው ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።


ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘ አደረገ፤ ማኅበሩም ሁሉ እያዩ ወደ ሖር ተራራ ወጡ።


እግዚአብሔር ወደሚሰጣቸው ምድር እንዳይሻገሩ የእስራኤልን ልጆች ልብ ለምን ታደክማላችሁ?


ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ በሄዱ ጊዜ፥ ምድሪቱንም ባዩ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ የእስራኤልን ልጆች ልብ አደከሙ።


እነርሱም ከሖር ተራራ ተጕዘው በሴልሞና ሰፈሩ።


እናንተ ግን ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።


እግዚአብሔርም እንዳለኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።


እስራኤልም በቃዴስ ተቀመጠ። በምድረ በዳም በኩል ሄዱ፥ የኤዶምያስንና የሞዓብንም ምድር ዞሩ፥ ከሞዓብ ምድርም በምሥራቅ በኩል መጡ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፥ አርኖንም የሞዓብ ድንበር ነበረና የሞዓብን ድንበር አላለፉም።


跟着我们:

广告


广告