Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 21:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ፤ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ከእጁ ወስዶ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሐሴቦን የቀድሞውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድሩን የወሰደበት የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ፤ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ከእጁ ወስዶ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሐሴቦን የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን መናገሻ ከተማ ነበረች፤ እርሱም ከሞአብ የቀድሞ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ወንዝ ያለውን ምድር ሁሉ ወስዶበት ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሐሴ​ቦ​ንም የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተማ ነበረ፤ እር​ሱም የፊ​ተ​ኛ​ውን የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ወግቶ ከአ​ሮ​ኤር እስከ አር​ኖን ድረስ ምድ​ሩን ሁሉ ወስዶ ነበር።

参见章节 复制




ዘኍል 21:26
13 交叉引用  

ሁለቱ ጡቶችሽ እንደ ሁለቱ መንታ እንደ ሚዳቋ ግለገሎች ናቸው።


አንገትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፥ ዓይኖችሽ በሐሴቦን ውስጥ በባትረቢ በር አጠገብ እንደ ውኃ ኵሬዎች ናቸው፥ አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አፋዛዥ እንደሚመለከት እንደ ሊባኖስ ግንብ ነው።


ከእንግዲህ ወዲህ የሞዓብ ትምክሕት የለም፥ በሐሴቦን ላይ፦ ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት ብለው ክፉ ነገር አስበውባታል። መድሜን ሆይ፥ አንቺ ደግሞ ትጠፊአለሽ ሰይፍም ያሳድድሻል።


ሞዓብም ፈርሶአልና አፈረ፥ አልቅሱ ጩኹም፥ ሞዓብ እንደ ተዘረፈ በአርኖን አጠገብ አውሩ።


የሸሹ ደክመው ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፥ እሳት ከሐሴቦን ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአል የሞዓብንም ማዕዘን የሤትንም ልጆች አናት በልቶአል።


እስራኤልም እነዚህን ከተሞች ሁሉ ወሰደ፤ እስራኤልም በአሞራውያን ከተሞች ሁሉ በሐሴቦንና በመንደሮቹ ሁሉ ተቀመጠ።


ስለዚህ በምሳሌ እንዲህ ተብሎ ተነገረ፦ ወደ ሐሴቦን ኑ። የሴዎን ከተማ ይሠራ፥ ይመሥረት፤


ድንበራቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥ የሜድባ ሜዳ ሁሉ፥


ሐሴቦንም፥ በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞትበኣል፥


ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በረባት ፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥


ሐሴቦንንና መሰምርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ።


እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አልወሰዳችኋቸውም ነበር?


跟着我们:

广告


广告