Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 21:23 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ ያልፍ ዘንድ እንቢ አለ፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ሴዎን ግን እስራኤል በግዛቱ ውስጥ እንዲያልፍ አልፈቀደም፤ ሰራዊቱን በሙሉ አሰባስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ወጣ፤ ያሀጽ እንደ ደረሰም ከእስራኤል ጋራ ጦርነት ገጠመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ሲሖን ግን የእስራኤል ሕዝብ በግዛቱ አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ እንዲያውም ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ በበረሓ ውስጥ ወዳለችው ወደ ያሀጽ በመሄድ በእስራኤላውያን ላይ ጦርነት አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሴዎ​ንም እስ​ራ​ኤል በወ​ሰኑ ላይ ያልፉ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለመ​ው​ጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፤ ወደ ኢያ​ሶ​ንም መጣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ተዋ​ጋ​ቸው።

参见章节 复制




ዘኍል 21:23
11 交叉引用  

ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮሁ ድምፃቸው እስከ ያሀፅ ድረስ ይሰማል፥ ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፥ ነፍስዋ በውስጥዋ ተንቀጠቀጠች።


በሜዳ ላይ፥ በሖሎን፥ በያሳ፥ በሜፍዓት ላይ፥


ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፥ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፥ የኔምሬም ውኃ ደግሞ ይደርቃል።


እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ኮምበል ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፥ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።


ኤዶምያስም፦ በሰይፍ እንዳልገጥምህ በምድሬ ላይ አታልፍም አለው።


ኤዶምያስም በብዙ ሕዝብና በጽኑ እጅ ሊገጥመው ወጣ። ኤዶምያስም እስራኤል በዳርቻው እንዳያልፍ ከለከለ፤ ስለዚህ እስራኤል ከእርሱ ተመለሰ።


ቤትባኣልምዖን፥ ያሀጽ፥ ቅዴሞት፥


ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ አላመነውም ነበር፥ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ በያሀጽም ሰፈረ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።


跟着我们:

广告


广告