Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 20:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሙሴና አሮንም ጉባኤውን በድንጋዩ ፊት ሰብስበው፦ እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚህ ድንጋይ ውኃን እናወጣላችኋለን? አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እርሱና አሮንም ማኅበሩን በዐለቱ ፊት አንድ ላይ ሰበሰቡ፤ ሙሴም፣ “እናንተ ዐመፀኞች ስሙ፤ ከዚህ ዐለት እኛ ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን?” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሙሴና አሮንም ጉባኤውን በድንጋዩ ፊት ሰበሰቡአቸው ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚህ ድንጋይ ውኃን እናውጣላችሁን?”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እርሱና አሮን መላውን ማኅበር በአለቱ ፊት ለፊት እንዲሰበሰቡ ካደረጉ በኋላ ሙሴ ሕዝቡን “እናንተ ዐመፀኞች! ከዚህ አለት ለእናንተ ውሃ እናውጣላችሁን?” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሙሴና አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን በዐ​ለቷ ፊት ሰብ​ስ​በው፥ “እና​ንተ ዓመ​ፀ​ኞች፥ እን​ግ​ዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚ​ህች ዐለት ውኃን እና​ወ​ጣ​ላ​ችሁ ነበር?” አሏ​ቸው።

参见章节 复制




ዘኍል 20:10
18 交叉引用  

እነርሱም፦ ሕልምን አልመን የሚተረጕምልን አጣን አሉት ዮሴፍም አላቸው፦ ሕልምን የሚተረጕም እግዚአብሔር የሰጠው አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ።


ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ ይህ በእኔ አይደለም እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በደኅንነት ይመልስለታል።


እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።


አሮን ወደ ወገኑ ይከማች፤ በመሪባ ውኃ ዘንድ በቃሌ ላይ ስለ ዓመፃችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባም።


እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።


እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም።


ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤


እናንተን ካወቅሁበት ቀን ጀምሮ በእግዚአብሔር ዓመፀኞች ነበራችሁ።


ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


跟着我们:

广告


广告