Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 18:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ለእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን አሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን የአሥራት አሥራት ታቀርባላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “ሌዋውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ርስት አድርጌ የምሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፣ እናንተም ካገኛችሁት ላይ አንድ ዐሥረኛ በማውጣት ለእግዚአብሔር መባ አድጋችሁ ታቀርባላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 “ለሌዋውያን ተናገር እነርሱንም እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእስራኤል ልጆች ለእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን አሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ለጌታ ለስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን የአሥራት አሥራት ታቀርባላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 “ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እግዚአብሔር ድርሻችሁ አድርጎ የሚሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፥ እናንተም በበኩላችሁ ከዚያው ከተቀበላችሁት የዐሥራት ዐሥራት በማውጣት ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 “ለሌ​ዋ​ው​ያን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ዐሥ​ራት በተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ እና​ን​ተ​ም​ከ​እ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ የዐ​ሥ​ራት ዐሥ​ራት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制




ዘኍል 18:26
7 交叉引用  

ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፥ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።


የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም የማንሣትን ቁርባንን የመቅደሱ ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፥ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።


መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ የማንሣት ቍርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ።


ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


የማንሣት ቍርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቈጠርላችኋል።


ከሌዊ ልጆችም ክህነትን የሚቀበሉት ከህዝቡ ማለት ከወንድሞቻቸው፥ እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ፥ ከእነርሱ አሥራትን በሕግ እንዲያስወጡ ትእዛዝ አላቸው፤


跟着我们:

广告


广告