Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 18:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከእህልም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እስራኤላውያን የመከር በኵራት አድርገው ለእግዚአብሔር የሚሰጡትን ምርጥ የወይራ ዘይት በሙሉ፣ ምርጥ የሆነውን አዲስ የወይን ጠጅና እህል ሁሉ ለእናንተ ሰጥቻችኋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ለጌታ ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከእህልም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “እስራኤላውያን የሚሰጡኝን ምርጥ የሆነ በኲራት፥ ይኸውም የወይራ ዘይት፥ የወይን ጠጅና እህል ለእናንተ እሰጣችኋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጡት የፍሬ መጀ​መ​ሪያ ከዘ​ይ​ትና ከወ​ይን ከስ​ን​ዴም የተ​መ​ረ​ጠ​ውን ሁሉ ለአ​ንተ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤

参见章节 复制




ዘኍል 18:12
19 交叉引用  

እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል ከምድርም የእህልንም የወይንንም ብዛት ይስጥህ አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ


አንድ ሰውም ከበኣልሻሊሻ የበኵራቱን እንጀራ፥ ሃያ የገብስ እንጀራ፥ የእህልም እሸት በአቁማዳ ይዞ ወደ እግዚአብሔር ሰው መጣ፤ እርሱም “ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው፤” አለ።


ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን ጠጅ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ ሁሉ በኵራት ሰጡ፤ የሁሉንም አሥራት አብዝተው አቀረቡ።


ነዶህንም የወይንህንም ጭማቂ ለማቅረብ አትዘግይ፤ የልጆችህንም በኵር ትሰጠኛለህ።


የተመረጠውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።


ጠቦቱን በእናቱ ወተት አትቀቅልም።


የበኵራቱ ሁሉ መጀመሪያ ከየዓይነቱ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፥ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የዱቄታችሁን በኵራት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።


እነዚህንም የበኵራት ቍርባን አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ እንደ ጣፋጭ ሽታ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠሉም።


ከበኵራትም የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ብታቀርብ ስለዚህ ቍርባን በእሳት የተጠበሰና የተፈተገ የእህል እሸት ታቀርባለህ።


ከየማደሪያችሁ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መልካም ዱቄት የተሠራ ሁለት የመወዝወዝ እንጀራ ታመጣላችሁ፤ ለእግዚአብሔር ለበኵራት ቍርባን እንዲሆን በእርሾ ይጋገራል።


ካህኑም ከበኵራቱ እንጀራ ከሁለቱም ጠቦቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ይወዘውዛቸዋል፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ፈንታ ነው፤ ለካህኑ ይሁን።


በሬ ወይም በግ ለመሥዋዕት ከሚያቀርቡት ሕዝብ የካህናቱ ወግ ይህ ይሆናል፤ ወርቹንና ሁለቱን ጉንጮቹን ጨጓራውንም ለካህኑ ይሰጣሉ።


የእህልህን የወይን ጠጅህን የዘይትህንም በኩራት፥ አስቀድሞም የተሸለተውን የበግህን ጠጉር ለእርሱ ትሰጣለህ።


አምላክህ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ፍሬ ሁሉ በኩራት ውሰድ በዕንቅብም አድርገው፥ አምላክህ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደ መረጠውም ስፍራ ይዘህ ሂድ።


የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ 2 ከጠቦት ስብ ጋር፥ 2 የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ 2 ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ 2 ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ።


跟着我们:

广告


广告