Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 17:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፥ ለመለመችም፥ አበባም አወጣች፥ የበሰለ ለውዝም አፈራች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በማግስቱም ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገባ በሌዊ ቤት ስም የቀረበችው የአሮን በትር ማቈጥቈጥ ብቻ ሳይሆን እንቡጥ አውጥታ፣ አብባና አልሙን አፍርታ አገኛት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እንዲህም ሆነ፤ በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነው የአሮን በትር አቈጥቁጦ፥ እምቡጥም አውጥቶ፥ አበባም አብቦ፥ የበሰለ ለውዝም አፍርቶ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በማግስቱ ሙሴ ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ በሌዊ ነገድ ስም የቀረበችው የአሮን በትር ለምልማ አገኛት፤ ይኸውም እንቡጥ አውጥታ በማበብ የበሰለ የለውዝ ፍሬ አፍርታ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆ​ነች የአ​ሮን በትር አቈ​ጠ​ቈ​ጠች፤ ለመ​ለ​መ​ችም፤ አበ​ባም አወ​ጣች፤ የበ​ሰለ ለው​ዝም አፈ​ራች።

参见章节 复制




ዘኍል 17:8
13 交叉引用  

በሕልሜ የወይን ዛፍ በፊቴ ሆና አየሁ በዛፊቱም ሦስት አረግ አለበት እርስዋም ቅጠልን አበባ አወጣች፥ ዘለላም አንጠለጠለች፥


በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በልጆች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም በጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው።


በዚያን ቀን የእግዚአብሔር ቍጥቋጥ ለጌጥና ለክብር ይሆናል፥ ከእስራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱ ፍሬ ለትምክሕትና ለውበት ይሆናል።


የዱር ዛፎች ሁሉ ረጅሙን ዛፍ ዝቅ ያደረግሁ፥ አጭሩንም ዛፍ ከፍ ያደረግሁ፥ የለመለመውንም ዛፍ ያደረቅሁ፥ የደረቀውንም ዛፍ ያለመለምሁ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ እኔም አድርጌአለሁ።


ነገር ግን በመዓት ተነቀለች ወደ መሬትም ተጣለች የምሥራቅም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፥ ብርቱዎች በትሮችዋም ተሰበሩና ደረቁ፥ እሳትም በላቻቸው።


ከጫፎችዋም በትሮች እሳት ወጣች ፍሬዋንም በላች፥ የነገሥታትም በትር ይሆን ዘንድ የበረታ በትር የለባትም። ይህ ሙሾ ነው፥ ለልቅሶም ይሆናል።


ለቆሬም ለወገኑም ሁሉ፦ ነገ እግዚአብሔር ለእርሱ የሚሆነውን፥ ቅዱስም የሚሆነውን ያስታውቃል፤ የመረጠውንም ሰው ወደ እርሱ ያቀርበዋል።


እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቍጣለች፥ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።


ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው፤ እነርሱም አዩ፥ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ።


በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበረ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፤ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ፥


跟着我们:

广告


广告