Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 16:42 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 እንዲህም ሆነ፤ ማኅበሩ በሙሴና በአሮን ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ ወደ መገናኛው ድንኳን አዩ፤ እነሆም፥ ደመናው ሸፈነው፥ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ማኅበሩም ሙሴንና አሮንን ለመቃወም በተሰበሰቡ ጊዜ ወደ መገናኛው ድንኳን ዘወር ሲሉ ደመና ድንኳኑን በድንገት ሸፍኖት አዩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 እንዲህም ሆነ፤ ማኅበሩ በሙሴና በአሮን ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ ወደ መገናኛው ድንኳን ዘወር ብለው ተመለከቱ፤ እነሆም፥ ደመናው ሸፈነው፥ የጌታም ክብር ተገለጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ሙሴንና አሮንን ለመቃወም ሁሉም በአንድነት ከተሰበሰቡ በኋላ ወደ መገናኛው ድንኳን ዞር ብለው ሲመለከቱ ደመናው የመገናኛውን ድንኳን ሸፍኖት የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ማኅ​በሩ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ከበ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ ደመ​ናው ሸፈ​ናት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለጠ።

参见章节 复制




ዘኍል 16:42
10 交叉引用  

እንዲህም ሆነ፤ አሮን ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በተናገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታቸውን አቀኑ፤ እነሆም የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ታየ።


የእግዚአብሔርንም ክብር ጥዋት ታያላችሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ያንጎራጎራችሁትን ሰምቶአልና በእኛም ላይ የምታንጎራጕሩ እኛ ምንድር ነን? አሉ።


የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ተቀመጠ፥ ደመናውም ስድስት ቀን ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።


ሙሴና አሮንም ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፤ ወጡም፥ ሕዝቡንም ባረኩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ።


ማኅበሩ ሁሉ ግን በድንጋይ ይወግሩአቸው ዘንድ ተማከሩ። የእግዚአብሔርም ክብር ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ተገለጠ።


ቆሬም ማኅበሩን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእነርሱ ላይ ሰበሰበ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለማኅበሩ ሁሉ ተገለጠ።


ሙሴና አሮንም ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት መጡ።


ለማኅበሩም ውኃ አልነበረም፤ በሙሴና በአሮንም ላይ ተሰበሰቡ።


ሙሴና አሮንም ከጉባኤው ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሂደው በግምባራቸው ወደቁ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው።


跟着我们:

广告


广告