Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 16:30 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እግዚአብሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ፈጽሞ አዲስ የሆነ ነገር አምጥቶ ምድር አፏን ከፍታ እነርሱንና የእነርሱ የሆነውን ሁሉ ብትውጥና በሕይወታቸው ወደ መቃብር ቢወርዱ፣ ሰዎቹ እግዚአብሔርን የናቁ መሆናቸውን የምታውቁት ያን ጊዜ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ጌታ ግን አንድ አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያንጊዜ እነዚህ ሰዎች ጌታን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ነገር ግን እግዚአብሔር ተሰምቶ የማይታወቅ አዲስ ነገር በመፍጠር በሕይወታቸው ሳሉ ወደ ሙታን ዓለም ይወርዱ ዘንድ ምድር ተከፍታ እነርሱንና የእነርሱ የሆነውን ሁሉ ብትውጥ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን የተቃወሙ መሆናቸውን ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈ​ጥር፥ ምድ​ርም አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱን፥ ቤታ​ቸ​ውን፥ ድን​ኳ​ና​ቸ​ውን፥ ለእ​ነ​ር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ ብት​ው​ጣ​ቸው፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውም ወደ ሲኦል ቢወ​ርዱ፥ ያን​ጊዜ እነ​ዚህ ሰዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ አስ​ቈጡ ታው​ቃ​ላ​ቸሁ።”

参见章节 复制




ዘኍል 16:30
12 交叉引用  

የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ከላይ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ርስት ከአርያም ምንድር ነው?


መዓትስ ለኃጢአተኛ፥ መለየትስ ለሚበድሉ አይደለችምን?


እግዚአብሔርም ሥራውን ማለት እንግዳ ሥራውን ይሠራ ዘንድ፥ አድራጎቱንም ማለት ያልታወቀውን አድራጎቱን ያደርግ ዘንድ በፐራሲም ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፥ በገባዖንም ሸለቆ እንደ ነበረ ይቈጣል።


እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፥ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ እናንተም አታውቁትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን አደርጋለሁ።


እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ፥ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።


ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ፥ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ፥ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።


አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፥ እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና ሴት ወንድን ትከብባለች።


እንዲህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መናገር በፈጸመ ጊዜ ከበታቻቸው ያለው መሬት ተሰነጠቀ፤


እነርሱም ለእነርሱም የነበሩ ሁሉ በሕይወታቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ።


跟着我们:

广告


广告