Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 16:28 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ሙሴም አለ፦ ይህን ሥራ ሁሉ አደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከኝ እንጂ ከልቤ እንዳይደለ በዚህ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሙሴም እንዲህ አለ፤ “እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንዳደርግ እግዚአብሔር እንደ ላከኝና ከራሴም እንዳይደለ በዚህ ታውቃላችሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ሙሴም እንዲህ አለ፦ “ይህን ሥራ ሁሉ ለመሥራት ጌታ ልኮኛል እንጂ ከልቤ አስቤው እንዳልሆነ በዚህ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በዚያን ጊዜ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህን ሁሉ ሥራ እንዳከናውን እግዚአብሔር እኔን የላከኝ መሆኑን የምታውቁትና እኔ ይህን ሁሉ ሥራ የማከናውነው በራሴ ፈቃድ እንዳልሆነ የምትገነዘቡት በዚህ ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ሙሴም አለ፥ “ይህን ሥራ ሁሉ አደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ላከኝ እንጂ ከልቤ እን​ዳ​ይ​ደለ በዚህ ታው​ቃ​ላ​ቸሁ።

参见章节 复制




ዘኍል 16:28
17 交叉引用  

የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ነቢዩ ኤልያስ ቀርቦ “አቤቱ፥ የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ! አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪያህ እንደ ሆንሁ፥ ይህንም ሁሉ በቃልህ እንዳደረግሁ ዛሬ ይገለጥ።


እርሱም፦ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ፤” አለ።


እንግዲህ አሁን ሂድ፤ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፤ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ፤” አለው።


አንተም ትናገረዋለህ፤ ቃሉንም በአፉ ታደርገዋለህ፤ እኔ ከአፍህና ከአፉ ጋር እሆናለሁ፤ የምታደርጉትንም አስተምራችኋለሁ።


“ፈርዖን፦ ‘ተአምራትን አሳዩኝ፤’ ሲላችሁ፥ አሮንን፦ ‘በትርህን ወስደህ እባብ እንድትሆን በፈርዖን ፊት ጣላት’ በለው”።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ፥ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል፥ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።


አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ከገዛ ልባቸው ትንቢት በሚናገሩ በሕዝብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊትህን አድርግ ትንቢትም ተናገርባቸው፥ እንዲህም በል፦


እነሆ፥ እጄን በላያቸው አወዛውዛለሁ፥ ተገዝተው ለነበሩት ብዝበዛ ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


የዘሩባቤል እጆች ይህን ቤት መሠረቱ፥ የእርሱም እጆች ይፈጽሙታል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ” አለ።


እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።


እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።


እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክር የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።


ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።


ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው።


跟着我们:

广告


广告