Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 15:28 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ኃጢአት ሠርቶ ሳያውቅ፥ ለሳተ ለዚያ ሰው ካህኑ ያስተሰርይለታል፤ በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፥ ይሰረይለትማል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ከዚያም ካህኑ፣ ባለማወቅ ኀጢአት ሠርቶ ለተሳሳተው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፤ ስርየት በሚደረግለትም ጊዜ ሰውየው ይቅር ይባላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ባለማወቅም ኃጢአት ሠርቶ ስሕተትን ለፈጸመው ለዚያ ሰው እንዲያስተሰርይለት፥ ካህኑ በጌታ ፊት ማስተስሪያ ያደርጋል፤ እርሱም ይቅር ይባላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ካህኑ በስሕተት ኃጢአት ለሠራው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተስርይለት፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ካህ​ኑም ባለ​ማ​ወቅ ስለ በደ​ለው ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ባለ​ማ​ወ​ቅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ስለ ሠራው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።

参见章节 复制




ዘኍል 15:28
5 交叉引用  

በካህኑም እጅ ውስጥ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያደርግበታል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል።


ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥


እንዲህም በወይፈኑ ያደርጋል፤ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት በታረደው ወይፈን እንዳደረገ እንዲሁ በዚህ ያደርጋል፤ ካህኑም ስለ እነርሱ ያስተሰርያል፥ እነርሱም ይቅር ይባላሉ።


ስቡ ሁሉ ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው ጠቦት ላይ እንደሚወሰድ ስብዋን ይወስዳል፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር በእሳት በተቃጠለው ቍርባን ላይ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።


ትውልዱ በእስራኤል ልጆች መካከል ቢሆን፥ ወይም በመካከላቸው የሚቀመጥ መጻተኛ ቢሆን፥ ሳያውቅ ኃጢአትን ለሚሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆንለታል።


跟着我们:

广告


广告