Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 13:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ወጡም ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ በሐማት ዳር እስካለችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ስለዚህ ወጥተው ከጺን ምድረ በዳ አንሥቶ በሌቦ ሐማት በኩል እስከ ረአብ ድረስ ዘልቀው ምድሪቱን አጠኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ወጡም ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ ለሌብ ሐማት ቅርብ እስከሆነችው እስከ ረዓብ ድረስ ሰለሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ስለዚህ ሰዎቹ ወደ ሰሜን ሄዱ፤ በአገሪቱም ከሚገኘው ከጺን ምድረ በዳ ጀምረው ለሐማት መተላለፊያ ቅርብ እስከሆነው ረሖብ ድረስ አጠኑ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ወጡም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ማት ዳር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።

参见章节 复制




ዘኍል 13:21
15 交叉引用  

የሐማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የአድርአዛርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ።


ስለ ደማስቆ፥ ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ ቀለጡም፥ በባሕርም ላይ ኅዘን አለ፥ ታርፍም ዘንድ አትችልም።


ንጉሡንም ይዘው የባቢሎን ንጉሥ ወዳለባት በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ አመጡት፥ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።


ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን።


ወደ ካልኔ አልፋችሁ ተመልከቱ፥ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፥ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፥ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን?


የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፥ በዚያም ተቀበረች።


እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው።


ከዔጽዮንጋብርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ናት።


ከሖርም ተራራ ወደ ሐማት መግቢያ ምልክት ታመለክታላችሁ የዳርቻውም መውጫ በጽዳድ ይሆናል፤


ሄዱም፥ ወደ ተራራማውም ወጡ፥ ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጥተው ጎበኙአት።


በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውኃ ስለ በደላችሁኝ፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል ስላልቀደሳችሁኝ፥


የጌባላውያንም ምድር፥ በምሥራቅም በኩል ከአርሞንዔም ተራራ በታች ካለችው በኣልጋድ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ያለችው ሊባኖስ ሁሉ፥


ለይሁዳም ልጆች ነገድ በየወገናቸው እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ዕጣ ሆነላቸው።


ከተማይቱ ከሲዶና ራቅ ያለች ነበረችና፥ እነርሱም ከሌሎች ሰዎች ተለይተው ብቻቸውን ይኖሩ ነበርና የሚታደግ አልነበራቸውም። ሌሳም በቤትሮዖብ አጠገብ ባለች ሸለቆ ውስጥ ነበረች። ከተማይቱንም ሠርተው ተቀመጡባት።


跟着我们:

广告


广告