Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 13:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጥቂቶች ወይም ብዙዎች እንደ ሆኑ፥ የሚኖሩባትም ምድር መልካም ወይም ክፉ፥ የሚኖሩባቸውም ከተሞች ሰፈሮች ወይም አምቦች እንደ ሆኑ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የሚኖሩባት ምድር ምን ዐይነት ናት? መልካም ወይስ መጥፎ? የሚኖሩባቸውስ ከተሞች ምን ይመስላሉ? በግንብ ያልታጠሩ ናቸው ወይስ የተመሸጉ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እንዲሁም የሚኖሩባት ምድር መልካም ወይም ክፉ፥ የሚኖሩባቸውም ከተሞች ሰፈሮች ወይም የተመሸጉ አምባዎች እንደ ሆኑ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ምድሪቱ መልካም ወይም መጥፎ እንደ ሆነች፥ ሕዝቡም የሚኖሩት ግልጥ በሆኑ መንደሮች ወይም በተመሸጉ ከተሞች እንደ ሆነ አጥኑ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር መል​ካም ወይም ክፉ፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ቅጥር ያላ​ቸው ወይም የሌ​ላ​ቸው እንደ ሆኑ፥

参见章节 复制




ዘኍል 13:19
3 交叉引用  

ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።


ምድሪቱንም እንዴት እንደ ሆነች፥ በእርስዋም የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፥


ምድሪቱም ወፍራም ወይም ስስ፥ ዛፍ ያለባት ወይም የሌለባት እንደ ሆነች እዩ፤ ከምድሪቱ ፍሬ አምጡ፤ አይዞአችሁ። በዚያን ጊዜም ወይኑ አስቀድሞ ፍሬ የሚያፈራበት ወራት ነበረ።


跟着我们:

广告


广告