Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 13:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሙሴም የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ላካቸው፥ አላቸውም፦ ከዚህ በደቡብ በኩል ውጡ፥ ወደ ተራሮችም ሂዱ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሙሴም ከነዓንን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ኔጌብን ዘልቃችሁ ወደ ተራራማው አገር ግቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሙሴም የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ላካቸው፥ እነርሱንም እንዲህ አላቸው፦ “ከዚህ በኔጌብ በኩል አድርጋችሁ ውጡ፥ ወደ ተራራማውም አገር ሂዱ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሙሴም ሲልካቸው እንዲህ አላቸው፦ “በኔጌብ በኩል አድርጋችሁ ወደ ተራራማው አገር ውጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ሙሴም የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ይሰ​ልሉ ዘንድ ላካ​ቸው፤ አላ​ቸ​ውም፥ “ከዚህ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ፥ ወደ ተራ​ሮ​ችም ውጡ።

参见章节 复制




ዘኍል 13:17
16 交叉引用  

አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ።


አብራምም ከግብፅ ወጣ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ።


ተነሣ በምድር በርዝመትዋም በስፋትዋም ሂድ እርስዋን ለአንተ እሰጣለሁና።


ከአዜብ ባደረገው በጉዞውም ወደ ቤቴል በኩል ሄደ ያም ስፍራ አስቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳን ተክሎበት የነበረው ነው፤


በሲዲም ሸለቆ ግን የዝፍር ጕድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥ የገሞራ ንጉሥም ሸሹ።


ምድሪቱንም እንዴት እንደ ሆነች፥ በእርስዋም የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፥


በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮቹም ኬጢያዊና ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ አጠገብ ተቀምጦአል።


በነጋውም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ ወጥተው፦ እነሆ፥ መጣን፤ እኛ በድለናልና እግዚአብሔር ወዳለው ስፍራ እንወጣለን አሉ።


በዚያም በተራራማው አገር ይኖሩ የነበር አሞራውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፥ ንብ እንደምታሳድድም አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር መቱአችሁ።


እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ተራራማውን አገር ደቡቡንም ቈላውንም ቁልቁለቱንም ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ መታ፥ ማንንም አላስቀረም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ወጣ፥ በሐጽሮንም በኩል አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥


የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ። ሄዱም፥ ረዓብም ወደሚሉአት ጋለሞታ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ።


እርስዋም፦ በረከትን ስጠኝ፥ በደቡብ በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና የውኃ ምንጭ ደግሞ ስጠኝ አለችው። ካሌብም ላይኛውንና ታችኛውን ምንጭ ሰጣት።


እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበረ፥ ይሁዳም ተራራማውን አገር ወረሰ፥ በሸለቆው የሚኖሩት ግን የብረት ሰረገሎች ነበሩአቸውና ሊያወጣቸው አልቻለም።


ከዚያም በኋላ የይሁዳ ልጆች በተራራማው አገርና በደቡብ በኩል በቈላውም ውስጥ የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ሊወጉ ወረዱ።


跟着我们:

广告


广告