Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 12:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰፈር ውጭ ተዘግታ ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔርም ለሙሴ፣ “አባቷ እፊቷ ላይ ቢተፋባት እስከ ሰባት ቀን በኀፍረት መቈየት አይገባትምን? አሁንም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን እንድትገለል አድርግ፤ ከዚያ በኋላ ግን ልትመለስ ትችላለች” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት እንኳ እርሷ ሰባት ቀን ልታፍር አይገባትምን? ሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጪ ተዘግቶባት ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ላይ ቢተፋባት እንኳ ኀፍረትዋን ተሸክማ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ትቈይ የለምን? ስለዚህም እርስዋ ከሰፈር ወጥታ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በገለልተኛ ቦታ ትቈይ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሳ ወደ ሰፈር ልትገባ ትችላለች።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራ​ቁን በፊቷ ቢተ​ፋ​ባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገ​ባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰ​ፈር ውጭ ተዘ​ግታ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመ​ለስ” አለው።

参见章节 复制




ዘኍል 12:14
13 交叉引用  

እግዚአብሔርም ንጉሡን ቀሠፈው፤ እስከሚሞትበትም ቀን ድረስ ለምጻም ሆነ፤ በተለየ ቤትም ይቀመጥ ነበር፤ የንጉሡም ልጅ ኢዮአታም በንጉሥ ቤት ላይ ሠልጥኖ ለአገሩ ሕዝብ ይፈርድ ነበር።


ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፥ በፊቱ ላይ ጺቅ እንደሚሉበት ሰው ሆንሁ።


ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ራቁ፥ አክታቸውንም በፊቴ መትፋትን አልተዉም።


ጀርባዬን ለገራፊዎች ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠሁ፥ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።


ቍቁቻውም በሥጋው ቁርበት ላይ ቢነጣ፥ ከቁርበቱም የጠለቀ ባይመስል፥ ጠጉሩም ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይዘጋበታል።


የነጻውም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ጠጕሩንም ሁሉ ይላጫል፥ በውኃም ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል። ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል፥ ነገር ግን ከድንኳኑ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


በዚያን ጊዜ በፊቱ ተፉበት፤ ጕኦሰሙትም፥ ሌሎችም በጥፊ መትተው፦ ክርስቶስ ሆይ፥ በጥፊ የመታህ ማን ነው?


ዋርሳይቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል ስትል ጭማውን ከእግሩ ታውጣ፥ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።


ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?


跟着我们:

广告


广告