Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የአሮንም ልጆች ካህናቱ መለከቶቹን ይንፉ፤ እነርሱም ለልጅ ልጃችሁ ለዘላለም ሥርዓት ይሁኑ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “መለከቶቹን ካህናቱ የአሮን ልጆች ይንፉ፤ ይህም ለእናንተና ለሚመጡት ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የአሮንም ልጆች ካህናቱ መለከቶቹን ይንፉ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 መለከቶቹን የሚነፉት ካህናቱ የአሮን ልጆች ይሆናሉ፤ ይህም ለልጅ ልጆቻችሁ የሚተላለፍ ቋሚ ሥርዓት ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ መለ​ከ​ቱን ይንፉ፤ ይህም ለልጅ ልጃ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።

参见章节 复制




ዘኍል 10:8
5 交叉引用  

ካህናቱም ሰበኒያ፥ ኢዮሣፍጥ፥ ናትናኤል፥ ዓማሣይ፥ ዘካርያስ፥ በናያስና አልዓዛር በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር። ዖቤድኤዶምና ይሒያም ለታቦቱ በረኞች ነበሩ።


ካህናቱም በናያስና የሕዚኤል በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ሁልጊዜ መለከት ይነፉ ነበር።


ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ሰደደ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ሰደዳቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም መለከት በእጁ ሰጠው።


跟着我们:

广告


广告