Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፥ በባሕሩም መካከል በደረቅ አለፉ፥ ጠላቶቻቸውን ግን ድንጋይ ለጥልቅ ውኃ እንዲጣል በቀላይ ውስጥ ጣልሃቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልህ፤ ያሳደዷቸውን ግን በኀይለኛ ውሃ ውስጥ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ውስጥ ወረወርሃቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፥ በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ተሻገሩ፤ አሳዳጆቻቸውን ግን በኃይለኛ ውኃ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ባሕሩን በፊታቸው ለሁለት ከፈልክ፤ በደረቅ ምድርም ተሻገሩ፤ ድንጋይ ወደ ጥልቅ ባሕር እንደሚጣል፥ እነርሱን ያሳድዱ የነበሩትንም ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከፊ​ታ​ቸ​ውም ባሕ​ሩን ከፈ​ልህ፤ በባ​ሕ​ሩም መካ​ከል በደ​ረቅ ዐለፉ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውን ግን ድን​ጋይ በጥ​ልቅ ውኃ እን​ዲ​ጣል በቀ​ላይ ውስጥ ጣል​ሃ​ቸው።

参见章节 复制




ነህምያ 9:11
16 交叉引用  

በደረቅ ምድር እንደሚያልፉ በኤርትራ ባሕር በእምነት ተሻገሩ፥ የግብፅ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ተዋጡ።


አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንስቶ ወደ ባሕር ወረወረው እንዲህ ሲል፦ ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።


ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤


እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤ እናንተም ዝም ትላላችሁ፤” አላቸው።


የሰረገሎቹንም መንኮራኵር አሰረ፤ ወደ ጭንቅም አገባቸው፤ ግብፃውያንም፦ “እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ፤” አሉ።


የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ ውስጥ በየብስ ሄዱ፤ ውኆችም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆኑላችው።


እስከ ዛሬም ድረስ ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብጽ ምድር ደግሞም በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች መካከል አድርገሃል፥ እንደ ዛሬም ለአንተ ስም አድርገሃል።


跟着我们:

广告


广告