Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 8:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ጸሐፊውም ዕዝራ ስለዚህ ነገር በተሠራ በእንጨት መረባርብ ላይ ቆሞ ነበር፥ በአጠገቡ መቲትያ፥ ሽማዕ፥ ዓናያ፥ ኦርዮ፥ ኬልቅያስ፥ መዕሤያ በቀኙ በኩል፥ ፈዳያ፥ ሚሳኤል፥ መልክያ፥ ሐሱም፥ ሐሽበዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሱላም በግራው በኩል ቆመው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ጸሓፊው ዕዝራ ለዚሁ ተብሎ በተሠራውና ከፍ ብሎ በሚገኘው የዕንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡም በስተ ቀኙ በኩል መቲትያ፣ ሽማዕ፣ ዓናያ፣ ኦርዮ፣ ኬልቅያስ፣ መዕሤያ፣ በስተ ግራው በኩል ደግሞ ፈዳያ፣ ሚሳኤል፣ መልክያ፣ ሐሱም፣ ሐሽበዳና፣ ዘካርያስና ሜሱላም ቆመው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጸሐፊውም ዕዝራ ለዚህ ተብሎ በተሠራ የእንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡ ማቲትያ፥ ሼማዕ፥ ዓናያ፥ ኡሪያ፥ ሒልቅያና ማዓሴያ በቀኙ በኩል፤ ፐዳያ፥ ሚሻኤል፥ ማልኪያ፥ ሐሹም፥ ሐሽባዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሹላም በግራው በኩል ቆመው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሕግ ምሁሩ ዕዝራ ለዚሁ ተግባር አመች ይሆን ዘንድ ከዕንጨት በተሠራ መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር በስተቀኙ በኩል የቆሙት ሰዎች ማቲትያ፥ ሼማዕ፥ ዓናያ፥ ኡሪያ፥ ሒልቂያና መዕሤያ ሲሆኑ፥ በስተ ግራው በኩል ደግሞ ፐዳያ፥ ሚሻኤል፥ ማልኪያ፥ ሐሹም፥ ሐሽባዳናህ፥ ዘካርያስና መሹላም ቆመው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር።

参见章节 复制




ነህምያ 8:4
16 交叉引用  

ከባኒ ልጆችም፤ ሜሱላም፥ መሉክ፥ ዓዳያ፥ ያሱብ፥ ሸዓል፥ ራሞት።


ከሐሱም ልጆችም፤ መትናያ፥ መተታ፥ ዛባድ፥ ኤሊፋላት፥ ይሬማይ፥ ምናሴ፥ ሰሜኢ።


ዓዙር፥ ሆዲያ፥ ሐሱም፥ ቤሳይ፥


ዓዛርያስ፥ ኤርምያስ፥ ፋስኮር፥ አማርያ፥ መልክያ፥


ሜሱላም፥ አብያ፥ ሚያሚን፥ መዓዝያ፥ ቤልጋል፥ ሸማያ፥ እነዚህ ካህናት ነበሩ።


የሴሎናዊውም ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ የዓዳያ ልጅ የዖዛያ ልጅ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ።


የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው፥ የየሻያ ልጅ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ የቆላያ ልጅ የፈዳያ ልጅ የዮእድ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ።


ከኤርምያስ ሐናንያ፥ ከዕዝራ ሜሱላም፥


በውኃውም በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ ወንዶችና ሴቶች የሚያስተውሉም ሲሰሙ፥ ከማለዳ ጀመሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፥ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ ለመስማት ያደምጥ ነበር።


ዕዝራም በሕዝቡ ሁሉ ላይ ከፍ ብሎ ሕዝቡ ሁሉ እያዩ መጽሐፉን ገለጠ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ።


በየስፍራቸውም ቆመው የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን የሕግ መጽሐፍ የቀን ሩብ ያህል አነበቡ ሦስት የቀን ሩብም ያህል ተናዘዙ፥ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም ሰገዱ።


ሌዋውያኑም ኢያሱና ባኒ፥ ቀድምኤል፥ ሰበንያ፥ ቡኒ፥ ሰራብያ፥ ባኒ፥ ክናኒ በደረጃዎች ላይ ቆመው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር በታላቅ ድምፅ ጮኹ።


ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።


跟着我们:

广告


广告