Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እርሱም፦ ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፥ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፥ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ነህምያም፣ “ሂዱ፤ ጥሩ ምግብ በመብላት፣ ጣፋጩን በመጠጣት ደስ ይበላችሁ፤ ምንም የተዘጋጀ ነገር ለሌላቸውም ካላችሁ ላይ ከፍላችሁ ላኩላቸው። ይህች ቀን ለጌታችን የተቀደሰች ናት፤ የእግዚአብሔር ደስታ ብርታታችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እርሱም፦ “ሂዱ፥ የሰባውን ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያ ምንም ላልተዘጋጀላቸው ድርሻቸውን ላኩ፤ ይህ ቀን ለጌታችን ቅዱስ ነውና፤ አትዘኑ የጌታ ደስታ ኃይላችሁ ነውና” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ነህምያ፦ “ሂዱና ምርጡን ምግብ ብሉ፤ ጣፋጩን መጠጥ ጠጡ፤ ምንም ለሌላቸውም ላኩ፤ ይህ ቀን ለአምላካችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ደስታ ኀይላችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።

参见章节 复制




ነህምያ 8:10
32 交叉引用  

በስምንተኛውም ቀን ሕዝቡን አሰናበተ፤ እነርሱም ንጉሡን መረቁ፤ እግዚአብሔርም ለባሪያው ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ በልባቸው ተደስተው ሐሤትም አድርገው ወደ ስፍራቸው ሄዱ።


ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኀይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው።


ሌዋውያንም፦ ቀኑ የተቀደሰ ነውና ዝም በሉ፥ አትዘኑም ብለው ሕዝቡን ሁሉ ጸጥ ያደርጉ ነበር።


ሕዝቡም ሁሉ የተነገረላቸውን ቃል አስተውለዋልና ሊበሉና ሊጠጡ እድል ፈንታም ሊሰድዱ ደስታም ሊያደርጉ ሄዱ።


ስለዚህም በመንደሮችና ባልተመሸጉ ከተሞች የሚኖሩ አይሁድ አዳር በሚባለው ወር አሥራ አራተኛውን ቀን የደስታና የመጠጥ የመልካምም ቀን፥ እርስ በርሳቸውም ስጦታ የሚሰጣጡበት ቀን ያደርጉታል።


አይሁድ ከጠላቶቻቸው ዕረፍትን ያገኙበት ቀን፥ ወሩም ከኀዘን ወደ ደስታ ከልቅሶም ወደ መልካም ቀን የተለወጠበት ወር ሆኖ ይጠብቁት ዘንድ፥ የግብዣና የደስታም ቀን፥ እርስ በርሳቸውም ስጦታ የሚሰጣጡበትና ለድሆች ስጦታ የሚሰጡበት ቀን ያደርጉት ዘንድ አዘዛቸው።


ለሰባት ደግሞም ለስምንት እድል ፈንታን ክፈል፥ በምድር ላይ የሚሆነውን ክፉ ነገር ምን እንደሆነ አታውቅምና።


ለሰው ከሚበላና ከሚጠጣ በድካሙም ደስ ከሚለው በቀር የሚሻለው ነገር የለም፥ ይህም ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።


ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።


እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፥ ይህ እድል ፈንታው ነውና።


እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ።


እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከሽቱዬ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮቼ ሆይ፥ ብሉ፥ ወዳጄ ሆይ፥ ጠጪ፥ እስክትረኪ ድረስ ጠጪ።


አሁንም በእግዚአብሔር ዓይን ከብሬአለሁና፥ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የሠራኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።


አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።


እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።


በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፥ የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ ከእነዚያም ወስደው ይቀቅሉባቸዋል፥ በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቤት ከነዓናዊው ከእንግዲህ ወዲያ አይገኝም።


ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።


በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል፤


እኔ ግን በሥጋ ደግሞ የምታመንበት አለኝ። ሌላ ሰው ማንም ቢሆን በሥጋ የሚታመንበት እንዳለው ቢመስለው፥ እኔ እበልጠዋለሁ።


እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስለ ሣቀዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል በደስታም ይኖራሉ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።


ጕልማሶችህን ጠይቃቸው፥ እነርሱም ይነግሩሃል፥ አሁንም እንግዲህ በመልካም ቀን መጥተንብሃልና ጕልማሶች በፊትህ ሞገስ ያግኙ፥ በእጅህም ከተገኘው ለባሪያዎችህና ለልጅህ ለዳዊት፥ እባክህ፥ ስጥ።


跟着我们:

广告


广告