Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አምላኬም ታላቆቹንና ሹማምቱን ሕዝቡንም ሰብስቤ እቈጥራቸው ዘንድ በልቤ አደረገ፥ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱንና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አምላኬም መኳንንቱን፥ ሹማምቱንና ሕዝቡን ሰብስቤ እንድቆጥራቸው በልቤ አስቀመጠ፤ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔርም ሕዝቡንና መሪዎቻቸው የሆኑ ባለሥልጣኖችን እንድሰበስብና የቤተሰባቸውን የትውልድ ሐረግ አመዘጋገብ እንድቈጣጠር አነሣሣኝ፤ ቀደም ባለው ጊዜ የተመለሱትንም ምርኮኞች የትውልድ ሐረግ ማስረጃ መዝገብ አገኘሁ፤ ያገኘሁትም ማስረጃ ከዚህ የሚከተለው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቤ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እቈ​ጥ​ራ​ቸው ዘንድ ልቤን አነ​ሣሣ፤ አስ​ቀ​ድ​መው የመ​ጡ​ት​ንም ሰዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐ​ፋ​ቸ​ውን አገ​ኘሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ደ​ዚህ ተጽፎ አገ​ኘሁ።

参见章节 复制




ነህምያ 7:5
15 交叉引用  

እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ።


በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያሳምር ዘንድ እንደዚህ ያለውን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥ በንጉሡ፥ በአማካሪዎቹና በንጉሡ ኃያላን አለቆች ሁሉ ፊት ምሕረቱን ወደ እኔ የላከ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። እኔም በላዬ ባለችው በአምላኬ በእግዚአብሔር እጅ በረታሁ፤ ከእኔም ጋር እንዲወጡ ከእስራኤል ዘንድ አለቆችን ሰበሰብሁ።


አምላኬ ሆይ፥ ለዚህ ሕዝብ ያድረግሁትን ሁሉ ለበጎነት አስብልኝ።


አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ሥራቸው ጦብያንና ሰንባላጥን ያስፈራሩኝም ዘንድ የወደዱትን ነቢይቱን ኖዓድያን የቀሩትንም ነቢያት አስብ።


ከተማይቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፥ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፥ ቤቶቹም አልተሠሩም ነበር።


እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፥ ከክህነትም ተከለከሉ።


ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።


ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤


ነገር ግን በቲቶ ልብ ስለ እናንተ ያንን ትጋት የሰጠ አምላክ ይመስገን፤


ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።


跟着我们:

广告


广告