Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፥ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹንም ካቆምሁ በኋላ፥ በረኞቹና መዘምራኑ ሌዋውያኑም ከተሾሙ በኋላ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ሆነ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ በሮቹን ካቆምሁ በኋላ፥ በር ጠባቂዎች፥ መዘምራንና ሌዋውያን ተሾሙ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እነሆ የቅጽሩ ግንብ ተሠርቶ አለቀ፤ የቅጽር በሮችም ሁሉ በየቦታቸው ተገጣጥመው ነበር፤ ቤተ መቅደሱን የሚጠብቁ ዘበኞች ለመዘምራን ቡድን አባላትና ለሌሎችም ሌዋውያን የሥራ ድርሻቸው ተመድቦላቸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተ​ሠራ በኋላ፥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አቆ​ምሁ፤ በረ​ኞ​ቹ​ንና መዘ​ም​ራ​ኑን፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ሾምሁ፤

参见章节 复制




ነህምያ 7:1
12 交叉引用  

መጥተውም “ወደ ሶርያውያን ሰፈር መጣን፤ እነሆም፥ ፈረሶችና አህዮች ታስረው፥ ድንኳኖችም ተተክለው ነበር እንጂ ሰው አልነበረም፤ የሰውም ድምፅ አልነበረም፤” ብለው ወደ ከተማይቱ ደጅ ጠባቂ ጮኹ።


ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው አቆመ፤ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፥ ያገለግሉም ዘንድ፥ ያመሰግኑም ያከብሩም ዘንድ ካህናቱንና ሌዋውያኑን አቆመ።


በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት፥ በሁለተኛውም ወር የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፥ የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ወንድሞቻቸው ካህናትና ሌዋውያን፥ ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት ምርኮኞች ሁሉ ጀመሩ፤ ሌዋውያንንም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ እንዲያሠሩት ሾሙአቸው።


የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም የማንሣትን ቁርባንን የመቅደሱ ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፥ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።


በኢየሩሳሌምም የተቀመጡት የአገሩ አለቆች እነዚህ ናቸው፥ እስራኤል ግን ካህናቱም ሌዋውያኑም ናታኒምም የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች እያንዳንዳቸው በየርስታቸውና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ተቀመጡ።


የሌዋውያኑም አለቆች ሐሸብያ፥ ሰራብያ፥ የቀድምኤልም ልጅ ኢያሱ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።


እንዲህም ሆነ፥ ቅጥሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍራሹም አንዳች እንዳልቀረበት ሰንበላጥና ጦብያ ዓረባዊውም ጌሳም የቀሩትም ጠላቶቻችን ሰሙ፥ ነገር ግን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን አላቆምሁም ነበር።


ቅጥሩም በኤሉል ወር በሀያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨረሰ።


ደግሞም በፊቴ ስለ እርሱ መልካም ይናገሩ ነበር፥ ቃሌንም ያወሩለት ነበር፥ ጦብያም ሊያስፈራራኝ ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር።


跟着我们:

广告


广告