Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፥ ቅጥሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍራሹም አንዳች እንዳልቀረበት ሰንበላጥና ጦብያ ዓረባዊውም ጌሳም የቀሩትም ጠላቶቻችን ሰሙ፥ ነገር ግን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን አላቆምሁም ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እስከዚያች ጊዜ ድረስ ለበሮቹ መዝጊያ ባልገጥምላቸውም እንኳ፣ ቅጥሩን መሥራቴንና የቀረ ክፍት ቦታ አለመኖሩን ሰንባላጥ፣ ጦቢያ፣ ዐረባዊው ጌሳምና የቀሩትም ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ሆነ ምንም እንኳ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን ባልገጥምም ቅጥሩን እንደሠራሁ፥ አንድም የፈረሰ እንዳልቀረ ሰንባላጥ፥ ጦቢያና ዓረባዊው ጌሼም የቀሩትም ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሰንባላጥ፥ ጦቢያ፥ ዐረባዊው ጌሼምና ሌሎችም ጠላቶቻችን የቅጽሩን ግንብ ሠርቼ መፈጸሜንና ያልተሠራ ክፍት ቦታ አለመኖሩን ሰሙ፤ ይሁን እንጂ በቅጽር በሮቹ ላይ መዝጊያዎችን አላቆምኩም ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥ​ሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍ​ራ​ሹም አን​ዳች እን​ዳ​ል​ቀ​ረ​በት ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦቢያ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም የቀ​ሩ​ትም ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሰሙ፤ ነገር ግን እስ​ከ​ዚያ ጊዜ ድረስ በበ​ሮቹ ውስጥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አላ​ቆ​ም​ሁም ነበር።

参见章节 复制




ነህምያ 6:1
10 交叉引用  

ከዚህም አስቀድሞ በአምላካችን ቤት ጓዳዎች ላይ ተሾሞ የነበረው ካህኑ ኤልያሴብ ከጦቢያ ጋር ተወዳጅቶ፥


ሖሮናዊውም ሰንባላጥና ባሪያው አሞናዊ ጦብያ ለእስራኤል ልጆች መልካምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበሳጩ።


ሖሮናዊውም ሰንባላጥ፥ ባሪያውም አሞናዊው ጦብያ፥ ዓረባዊዉም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በንቀት ሳቁብን፤ ቀላል አድርገውንም፦ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድር ነው? በውኑ በንጉሡ ላይ ትሸፍቱ ዘንድ ትወድዳላችሁን?” አሉ።


ታላቁም ካህን ኤልያሴብ ወንድሞቹም ካህናት ተነሥተው የበግ በር ሠሩ፥ ቀደሱትም፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ እስከ ሃሜአ ግንብና እስከ ሐናንኤል ግንብ ድረስ ቀደሱት።


የሃስናአ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ፥ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ።


የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም አሮጌውን በር አደሱ፥ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ።


ሰንባላጥም ቅጥሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፥ ተበሳጨም፥ በአይሁድም አላገጠ።


እንዲህም ሆነ፥ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹንም ካቆምሁ በኋላ፥ በረኞቹና መዘምራኑ ሌዋውያኑም ከተሾሙ በኋላ፥


ስለዚህ እወቅ አስተውልም፥ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፥ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።


跟着我们:

广告


广告