Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አያሌዎቹም፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ብዙዎች ናቸው፥ በልተንም በሕይወት እንድንኖር እህልን እንሸምት ይሉ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንዳንዶቹ፣ “እኛም ሆነ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን በቍጥር ብዙ ነን፤ ታዲያ ለመብላትም ሆነ በሕይወት ለመቈየት እህል ማግኘት አለብን” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እንዲህ የሚሉ ነበሩ፦ “እኛ፥ ወንዶች ልጆቻችንና ሴቶች ልጆቻችን ብዙ ነን፤ እንድንበላና በሕይወት እንድንኖር እህልን እንውሰድ”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከእነርሱም አንዳንዶቹ “ብዙ ቤተሰብ ስላለን ሕይወታችንን ለማትረፍ የሚያስችለን እህል እንፈልጋለን” አሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር ብዙ​ዎች ነን፤ በል​ተ​ንም በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ን​ኖር እህ​ልን እን​ሸ​ምት” የሚሉ ነበሩ።

参见章节 复制




ነህምያ 5:2
11 交叉引用  

አገሮችም ሁሉ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወደ ዮሴፍ መጡ በምድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበርና።


እንዲህም አለ፦ እነሆ ስንዴ በግብፅ እንዲገኝ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚይ ውረዱ፥ እንድንድንና እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን።


ይሁዳም አባቱን እስራኤልን አለው፦ እኛና አንተ ልጆቻችንም ደግሞ እንድንድን እንዳንሞትም ብላቴናውን ከእኔ ጋር ስደደው እናም ተንሥተን እንሄዳለን።


ምድራችንስ ስለ ምን ትጠፋለች? እኛንም ምድራችንንም በእህል ግዛን እኛም ለፈርዖን ባሪያዎች እንሁን ምድራችንም ለእርሱ ትሁን እኝ እንድንድን እንዳንሞትም ምድራችንም እንዳትጠፋ ዘር ስጠን።


ከነቢያትም ወገን ሚስቶች አንዲት ሴት “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን ይፈራ እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳ ሁለት ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል፤” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።


አያሌዎቹም፦ ከራብ የተነሣ እህልን እንሸምት ዘንድ እርሻችንና ወይናችንን ቤታችንንም አስይዘናል ይሉ ነበር።


ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፥ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፥ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፥ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፥ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።


ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድዳባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፥ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።


ለወንድምህ በወለድ አታበድር፤ የብር ወይም የእህል ወይም የማናቸውንም ነገር ሁሉ ወለድ አትውሰድ።


跟着我们:

广告


广告