Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 4:23 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እኔና ወንድሞቼም ብላቴኖቼም በኋላዬም የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እኔም ሆንሁ ወንድሞቼ፣ ሰዎቼም ሆኑ ከእኔ ጋራ ያሉት ጠባቂዎች ልብሳችንን አላወለቅንም፤ ለውሃ እንኳ በምንሄድበት ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የጦር መሣሪያውን እንደ ያዘ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እኔም ሆንኩ የሥራ ጓደኞቼ፥ አገልጋዮቼም ሆኑ የክብር ዘቦቼ፥ ሁላችንም ሌሊት እንኳ ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። በዚህም ዐይነት ውሃ ስንቀዳ እንኳ መሣሪያችን ከእጃችን አልተለየም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እኔና ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በኋ​ላ​ዬም የነ​በ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች ልብ​ሳ​ች​ንን አና​ወ​ል​ቅም ነበር። ወደ ውኃም ስን​ሄድ መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን እን​ደ​ታ​ጠ​ቅን እን​ሄድ ነበር።

参见章节 复制




ነህምያ 4:23
8 交叉引用  

ደግሞም በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፦ ሁላችሁ ከብላቴኖቻችሁ ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ እደሩ፥ በሌሊትም ጠባቂዎች ሁኑልን፥ በቀንም ሥሩ አልኋቸው።


በወንድሞቻቸውም በአይሁድ ላይ ትልቅ የሕዝቡና የሚስቶቻቸው ጩኸት ሆነ።


ደግሞም አጥብቄ የቅጥሩን ሥራ ሠራሁ፥ እርሻም አልገዛንም፥ ብላቴኖቼም ሁሉ ወደዚያው ወደ ሥራው ተሰበሰቡ።


ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፥ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።


አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በሰልፍ መካከል ያልፋሉ፥ እነርሱም አይቈስሉም።


ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።


በማጠጫው መካከል ካሉት ከቀስተኞች ጩኸት ርቀው፥ በዚያ የእግዚአብሔርን ጽድቅ፥ በእስራኤል ላይ የግዛቱን ጽድቅ ይጫወታሉ፥ ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ በሮች ወረዱ።


አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር ያሉትም ሕዝብ ሁሉ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጡ፥ አቤሜሌክም በእጁ መጥረቢያ ወስዶ የዛፉን ቅርንጫፍ ቈረጠ፥ አንሥቶም በጫንቃው ላይ አደረገው፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሕዝብ፦ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን፥ እናንተም ፈጥናችሁ እኔ እንዳደረግሁ አድርጉ አላቸው።


跟着我们:

广告


广告