Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 4:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሥራውንም ሠራን ከማለዳ ወገግታም ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ እኩሌቶቹ ጦር ይይዙ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ስለዚህ ጎሕ ሲቀድ ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ እኩሌቶቹ ሰዎች ጦራቸውን እንደ ያዙ ሥራውን ቀጠልን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ስለዚህም በየቀኑ ከማለዳ ጀምሮ በምሽት፥ ከዋክብት እስከሚወጡበት ጊዜ ድረስ እኩሌቶቹ ሲሠሩ፥ እኩሌቶቹ መሣሪያ ታጥቀው ዘብ በመቆም ይጠብቁ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሥራ​ው​ንም እን​ሠራ ነበር፤ ከማ​ለዳ ወገ​ግ​ታም ጀምሮ ከዋ​ክ​ብት እስ​ኪ​ወጡ ድረስ እኩ​ሌ​ቶቹ ጦር ይይዙ ነበር።

参见章节 复制




ነህምያ 4:21
6 交叉引用  

የቀንደ መለከቱን ድምፅ ወደምትሰሙበት ስፍራ ወደዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፥ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል አልኋቸው።


ደግሞም በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፦ ሁላችሁ ከብላቴኖቻችሁ ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ እደሩ፥ በሌሊትም ጠባቂዎች ሁኑልን፥ በቀንም ሥሩ አልኋቸው።


ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።


ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።


ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።


ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ።


跟着我们:

广告


广告