Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፦ እነዚህ ደካሞች አይሁድ የሚሠሩት ምንድር ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን? ብሎ ተናገረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በተባባሪዎቹና በሰማርያ ሰራዊት ፊት፣ “እነዚህ ደካማ አይሁድ ምን እያደረጉ ነው? ቅጥራቸውን መልሰው ሊሠሩ ነውን? መሥዋዕት ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት ጀንበር ሠርተው ሊጨርሱ ነውን? እንደዚያ ተቃጥሎ የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን?” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 መጥተው ኢየሩሳሌምን ሊወጉና ሊሸብሩ ሁሉም በአንድነት አሴሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በጓደኞቹና በሰማርያ ወታደሮች ፊት “እነዚህ ደካሞች አይሁድ ምን ለማድረግ አስበዋል? ከተማይቱን እንደገና መልሰው ለመሥራት ዐቅደዋልን? መሥዋዕት በማቅረብስ ሥራውን በአንድ ቀን ለመፈጸም የሚችሉ ይመስላቸዋልን? ለግንብ የሚሆኑ ድንጋዮችንስ ከተቃጠለው ፍርስራሽ ክምር ውስጥ ማውጣት ይችሉ ይሆን?” ሲል በመዘበት ተናገረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በወ​ን​ድ​ሞ​ቹና በሰ​ማ​ርያ ሠራ​ዊ​ትም ፊት፥ “ከተ​ማ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ እነ​ዚህ ደካ​ሞች አይ​ሁድ ኀይ​ላ​ቸው ምን​ድን ነው? ይተ​ዉ​ላ​ቸ​ዋ​ልን? ይሠ​ዋ​ሉን? በአ​ንድ ቀንስ ይጨ​ር​ሳ​ሉን? የተ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንስ ድን​ጋይ ከፍ​ር​ስ​ራሹ መል​ሰው ያድ​ኑ​ታ​ልን?” ብሎ ተና​ገረ።

参见章节 复制




ነህምያ 4:2
17 交叉引用  

የምድሩም ሕዝብ የይሁዳን ሕዝብ እጅ ያደክሙ ነበር፤ እንዳይሠሩም አስፈራሩአቸው፤


የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርም በጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።


እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፥ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፥ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ።


ይሁዳም፦ የተሸካሚዎች ኃይል ደከመ፥ ፍርስራሹም ብዙ ነው፥ ቅጥሩንም እንሠራ ዘንድ አንችልም አሉ።


ቅጥሩም በኤሉል ወር በሀያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨረሰ።


ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነቢይ ነበረ፥ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል ብሎ ተናገረ።


ይህ ሕዝብ፦ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁለቱን ወገን ጥሎአቸዋል ያለውን ነገር አትመለከትምን? እንዲሁ በፊታቸው ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ እንዳይሆን ሕዝቤን አቃልለዋል።


ስለዚህ እወቅ አስተውልም፥ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፥ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።


አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፥ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፥ በዓመታት መካከል ትታወቅ፥ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።


በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፥ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፥ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።


የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፥ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።


ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤


跟着我们:

广告


广告