Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 4:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሰንባላጥም ቅጥሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፥ ተበሳጨም፥ በአይሁድም አላገጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሰንባላጥ ቅጥሩን እንደምንሠራ በሰማ ጊዜ ተቈጣ፤ እጅግም ተበሳጨ። በአይሁድም ላይ ተሣለቀ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሳንበላጥ፥ ጦብያ፥ ዓረባውያን፥ አሞናውያንና አሽዶዳውያን የሚታደሰው የኢየሩሳሌም ቅጥር ከፍ እያለ እንደ ሄደ፥ የፈረሰውም እየተጠገነ እንደሆነ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እኛ አይሁድ የቅጽሩን ግንብ ሥራ መጀመራችንን ሰንባላጥ በሰማ ጊዜ በጣም ተቈጣ፤ ተበሳጭቶም ሊዘባበትብን ተነሣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሰን​ባ​ላ​ጥም ቅጥ​ሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ተበ​ሳ​ጨም፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ሳቀ​ባ​ቸው።

参见章节 复制




ነህምያ 4:1
13 交叉引用  

ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ ለሖሮናዊው ለሰንበላጥ አማች ነበረ፥ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።


ሖሮናዊውም ሰንባላጥና ባሪያው አሞናዊ ጦብያ ለእስራኤል ልጆች መልካምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበሳጩ።


ሖሮናዊውም ሰንባላጥ፥ ባሪያውም አሞናዊው ጦብያ፥ ዓረባዊዉም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በንቀት ሳቁብን፤ ቀላል አድርገውንም፦ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድር ነው? በውኑ በንጉሡ ላይ ትሸፍቱ ዘንድ ትወድዳላችሁን?” አሉ።


ቅጥሩም በኤሉል ወር በሀያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨረሰ።


ጠላቶቻችንም ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፥ በራሳቸውም አሳብ እጅግ ተዋረዱ፥ ይህም ሥራ በእግዚአብሔር እንደ ተደረገ አወቁ።


ንጉሡም ሴዴቅያስ ኤርምያስን፦ ወደ ከለዳውያን በኰበለሉት በአይሁድ እጅ አሳልፈው ይሰጡኛል እነርሱም ያፌዙብኛል ብዬ እፈራለሁ አለው።


ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።


ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው፦ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤


ሊቀ ካህናቱ ግን የሰዱቃውያን ወገን ሆነውም ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ተነሡ ቅንዓትም ሞላባቸው።


ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤


跟着我们:

广告


广告