Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ንጉሡንም፦ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ! የአባቶቼ መቃብር ያለባት ከተማ ተፈትታለችና፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋልና ፊቴ ስለ ምን አይዘን?” አልሁት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ለንጉሡም “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር፤ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ስትፈርስ፣ በሮቿም በእሳት ሲቃጠሉ ለምን ፊቴ አይዘን?” አልሁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ንጉሡንም እንዲህ አልሁት፦ “ንጉሡ ለዘለዓለም ይኑር! የአባቶቼ መቃብር ያለባት ከተማ ስትፈርስ፥ በሮችዋም በእሳት ሲቃጠሉ ፊቴ ለምን አያዝን?”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “ንጉሠ ነገሥቱ ለዘለዓለም ይኑር! የቀድሞ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፍርስራሽ ሆና ስትቀርና የቅጽሮችዋም በሮች በእሳት ሲወድሙ እንዴት አላዝንም?” ስል መለስኩለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኑር፤ የአ​ባ​ቶች መቃ​ብር ያለ​ባት ከተማ ተፈ​ት​ታ​ለ​ችና፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና ፊቴ ስለ ምን አያ​ዝን?” አል​ሁት።

参见章节 复制




ነህምያ 2:3
21 交叉引用  

ቤርሳቤህም በግምባርዋ በምድር ላይ ተደፍታ ለንጉሡ እጅ ነሣችና “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም በሕይወት ይኑር!” አለች።


በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ባሪያ የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።


መንገሥም በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ሁለት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያዝንለት ሄደ፤ በዳዊትም ከተማ እንጂ በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።


አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በከተማይቱም በኢየሩሳሌም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላገቡትም፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።


ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ልጆች መቃብር በላይኛው ክፍል ቀበሩት፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ በሞቱ አከበሩት። ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።


የእግዚአብሔርንም ቤት አቃጠሉ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ፤ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠሉ፤ መልካሙንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፉ።


እነርሱም፦ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፤ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።


በሸለቆውም በር ወጣሁ፤ ወደ ዘንዶውም ምንጭና ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄድሁ፤ የፈረሰውንም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፥ በእሳትም የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትሁ።


እኔ በሕዝቤ ላይ የሚወርደውን ክፉ ነገር አይ ዘንድ እንዴት እችላለሁ? ወይስ የዘመዶቼን ጥፋት አይ ዘንድ እንዴት እችላለሁ? አለች።


በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በአሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የቆመው የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።


ጤት። በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፥ መወርወሪያዎችዋን አጠፋ ሰበረም፥ ንጉሥዋና አለቆችዋ ሕግ በሌለባቸው በአሕዛብ መካከል አሉ፥ ነቢያቶችዋም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላገኙም።


ከለዳውያኑም ንጉሡን በሶርያ ቋንቋ፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ፥ ለባሪያዎችህ ሕልምህን ንገር፥ እኛም ፍቺውን እናሳይሃለን ብለው ተናገሩት።


ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።


ንግሥቲቱም ስለ ንጉሡና ስለ መኳንንቱ ቃል ወደ ግብዣ ቤት ገባች፥ ንግሥቲቱም ተናገረች እንዲህም አለች፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ፥ አሳብህ አያስቸግርህ፥ ፊትህም አይለወጥ።


ዳንኤልም ንጉሡን፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።


የዚያን ጊዜም አለቆቹና መሳፍንቱ ወደ ንጉሡ ተሰብስበው እንዲህ አሉት፦ ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።


ከተሞቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፥ መቅደሶቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ መልካሙንም መዓዛችሁን አላሸትትም።


跟着我们:

广告


广告