Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አድርጌለሁ? በምንስ አድክሜሃለሁ? መስክርብኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “ሕዝቤ ሆይ፤ ምን አድርጌሃለሁ? ሸክም የሆንሁብህስ እንዴት ነው? እስኪ መልስልኝ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አደረግሁህ? ያደከምኩህስ እንዴት ነው? መልስልኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕዝቤ ሆይ! ምን አደረግሁህ? ያከበድኩብህስ ነገር ምንድን ነው? እስቲ መልስልኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አድርጌለሁ? በምንስ አድክሜሃለሁ? መስክርብኝ።

参见章节 复制




ሚክያስ 6:3
11 交叉引用  

ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስተማመን ስለምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?


ትውልድ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ተመልከቱ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንሁባትን? ሕዝቤስ ስለ ምን፦ እኛ ፈርጥጠናል፥ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል?


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከንቱነትንም የተከተሉ፥ ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው?


ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።


አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፤


跟着我们:

广告


广告