Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አሁን፦ ተነሣ፥ በተራሮችም ፊት ተፋረድ፥ ኮረብቶችም ቃልህን ይስሙ ብሎ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ፤ “ተነሡ፤ ጕዳያችሁን በተራሮች ፊት አቅርቡ፤ ኰረብቶች እናንተ የምትሉትን ይስሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ የሚለውን ስሙ፥ ተነሥ፥ በተራሮች ፊት ክርክራችሁን አቅርቡ፥ ኮረብቶች ቃልህን ይስሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ የሚናገረውን ስሙ፤ ተነሡ! ያላችሁን ቅርታ በተራሮች ፊት አቅርቡ! ኰረብቶችም የምትሉትን ይስሙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አሁን፦ ተነሣ፥ በተራሮችም ፊት ተፋረድ፥ ኮረብቶችም ቃልህን ይስሙ ብሎ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ።

参见章节 复制




ሚክያስ 6:1
22 交叉引用  

እግዚአብሔር ተናግሮአልና ሰማያት ስሙ፥ ምድርም አድምጪ፥ ልጆችን ወለድሁ አሳደግሁም፥ እነርሱም አመጹብኝ።


እግዚአብሔር ለፍርድ ተነሥቶአል በሕዝቡም ላይ ሊፈርድ ቆሞአል።


ስሙ፥ አድምጡ፥ እግዚአብሔር ተናግሮአልና አትታበዩ።


ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ።


አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናግረህ፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በል።


የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ እናንተ ግን ቅርንጫፎቻችሁን ታቈጠቍጣላችሁ፥ ይመጡም ዘንድ ቀርበዋልና ለሕዝቤ ለእስራኤል ፍሬአቸሁን ትሰጣላችሁ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ።


እንዲህም በል፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች ለምንጮችና ለሸለቆች እንዲህ ይላል፦ እኔ፥ እነሆ፥ እኔ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ የኮረብታው መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ።


የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር በእናንተ፥ ከግብጽ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፥


እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ ስሙ፥ ምድርም ሙላዋም ታድምጥ፥ ጌታ እግዚአብሔርም፥ እርሱም በቅዱስ መቅደሱ የሆነ ጌታ፥ ይመስክርባችሁ።


ተራሮችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ በገደልም ወርዶ እንደሚፈስስ ውኃ፥ በበታቹ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆችም ይሰነጠቃሉ።


ባልሰሙም አሕዛብ ላይ በቍጣና በመዓት እበቀላለሁ።


ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።


መልሶም፦ እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው።


ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤ 2 ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ።


ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ አስመሰክራለሁ፤ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረጅም ዘመን አትቀመጡባትም።


አሁንም እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ስላደረገው ጽድቅ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እምዋገታችሁ ዘንድ በዚህ ቁሙ።


ሳሙኤልም ሳኦልን፦ ቆይ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ አለው፥ እርሱም፦ ተናገር አለው።


跟着我们:

广告


广告