Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁንስ ከከተማ ወጥተሽ፣ በሜዳ ላይ መስፈር አለብሽና፤ ወደ ባቢሎን ትሄጃለሽ፤ በዚያ ከጠላት እጅ ትድኛለሽ። እግዚአብሔር በዚያ፣ ከጠላቶችሽ ይታደግሻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጪ፥ ተጨነቂ፤ አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትቀመጫለሽና፥ ወደ ባቢሎንም ትሄጃለሽ፤ በዚያ ትድኛለሽ፥ በዚያም ጌታ ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት እየቃተታችሁ ተንፈራፈሩ፤ ከከተማ ተባራችሁ በሜዳ ላይ ትሰፍራላችሁ ወደ ባቢሎንም ትሄዳላችሁ፤ ይሁን እንጂ በዚያ እግዚአብሔር ያድናችኋል፤ ከጠላቶቻችሁም እጅ ይታደጋችኋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።

参见章节 复制




ሚክያስ 4:10
27 交叉引用  

ከአንተም ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ፤” አለው።


ከተማይቱም ተሰበረች፤ ሰልፈኞችም ሁሉ በሁለት ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ሸሹ፤ ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓረባም መንገድ ሄዱ።


ስለዚህም እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አለቆች አመጣባቸው፤ ምናሴንም በዛንጅር ያዙት፤ በሰንሰለትም አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት።


ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባሪያዎች ሆኑ፤


‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እሠራለት ዘንድ አዝዞኛል፤ ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም ይውጣ’” ብሎ በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ አስነገረ፤ ደግሞም በጽሕፈት አደረገው።


የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፥ ከላዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።


እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፥ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ከባቢሎን ውጡ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፥ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ ይህንም ንገሩ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፦ እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ታድጎታል በሉ።


ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፥ ከጨካኞችም ጡጫ እቤዥሃለሁ።


ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኋችሁ ምርኮኞች ሁሉ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


እንደምታምጥ የበኵርዋንም እንደምትወልድ ሴት ድምፅ ሰምቻለሁና፥ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ይሰልላል፥ እጆችዋንም ትዘረጋለችና፦ ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።


ከተሞቹ ተይዘዋል፥ አምባዎቹም ተወስደዋል፥ በዚያም ቀን የሞዓብ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።


የባቢሎንም ንጉሥ መታቸው፥ በሐማትም ምድር ባለችው በሪብላ ገደላቸው። እንዲሁ ይሁዳ ከአገሩ ተማረከ።


ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፥ በሚወለድበት ጊዜ በማኅፀን አፍ ቀጥ ብሎ አይወጣምና አእምሮ የሌለው ልጅ ነው።


እርስዋም፦ ውሽሞቼ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፥ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።


አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ የቀሩትም ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።


ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።


跟着我们:

广告


广告