Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ነቢያቶቻቸው፣ “ትንቢት አትናገርብን፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር፤ ውርደት አይደርስብንም” ይላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “አትስበኩ” ብለው ይሰብካሉ፤ “ስለ እነዚህ ነገሮች መስበክ የለባችሁም፤ ውርደት አይደርስብንም።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የእነርሱ ነቢያት “ትንቢት አትናገር፤ እንደዚህ ያለው ውርደት የማይደርስብን ስለ ሆነ ስለ ነዚህ ጉዳዮች ትንቢት አትናገር” ይሉኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም።

参见章节 复制




ሚክያስ 2:6
21 交叉引用  

እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል።


ባለ ራእዮችን፦ አትመልከቱ ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፥


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ደቡብ አቅና ወደ ደቡብም ተናገር በደቡብም ባለው ዱር ላይ ትንቢት ተናገር፥


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አቅና ወደ መቅደሶችም ተናገር በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር።


እኔም ምላስህን ከትናጋህ ጋር አጣብቃታለሁ አንተም ዲዳ ትሆናለህ፥ እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና የሚዘልፍ ሰው አትሆንባቸውም።


እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፥ ነቢያቱንም፦ ትንቢትን አትናገሩ ብላችሁ አዘዛችኋቸው።


በዚያም ትንቢትን ተናገር፥ ነገር ግን ቤቴል የንጉሥ መቅደስና የመንግሥት ቤት ናትና ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትንቢት አትናገር አለው።


አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፥ አንተ፦ በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ ብለሃል፥


ስለዚህ ሌሊት ይሆንባችኋል እንጂ ራእይ አይሆንላችሁም፥ ጨለማም ይሆንባችኋል እንጂ አታምዋርቱም፥ ፀሐይም በነቢያት ላይ ትገባለች፥ ቀኑም ይጠቁርባቸዋል።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ አብዝቶ እንዳይስፋፋ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው” ብለው እርስ በርሳቸው ተማከሩ።


ሊቀ ካህናቱም፦ “በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን? እነሆም፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ” ብሎ ጠየቃቸው።


ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።


እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።


跟着我们:

广告


广告