Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት ላመጣ ዐቅጃለሁ፤ ከዚህም ለማምለጥ አትችሉም። ከእንግዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤ የመከራ ጊዜ ይሆናልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በዚህ ቤተሰብ ላይ ክፉ አቅጃለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን ማውጣት አትችሉም፤ በትዕቢትም አትሄዱም፥ ጊዜው ክፉ ነውና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ በእናንተ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፤ ከዚህም ልታመልጡ ፈጽሞ አትችሉም፤ ያ አሠቃቂ ጊዜ ስለሚሆን በትዕቢት መመላለስ አትችሉም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።

参见章节 复制




ሚክያስ 2:3
29 交叉引用  

ጨካኙ ሰው አልቆአልና፥ ፌዘኛውም ጠፍቷልና፥ ለኃጢአትም የደፈጡ ሁሉ ይቈረጣሉና፥


ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የጽዮን ቈነጃጅት ኮርተዋልና፥ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፥ ፈንጠርም እያሉ፥ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉና


ሥራውንም ያፋጥን፥ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር ትቅረብ፥ ትምጣ ለሚሉ ወዮላቸው!


አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፥ አሳብንም አስብባችኋለሁ፥ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው።


ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም በዚህ ቃል ተናገርሁ፦ ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉ ለእርሱና ለሕዝቡም ተገዙላቸው በሕይወትም ኑሩ።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው የአርነት አዋጅ ለመንገር እኔን አልሰማችሁም፥ እነሆ፥ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር ለራብም የአርነት አዋጅ እናገርባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል እንድትበተኑ አደርጋችኋለሁ።


ይሁዲም ሦስት ወይም አራት ዓምድ ያህል ባነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ በካራ ቀደደው፥ ክርታሱም በምድጃ ውስጥ ባለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ጣለው።


የሆሻያ ልጅ ዓዛርያስ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፦ ሐሰት ተናግረሃል፥ አምላካችን እግዚአብሔር፦ በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብጽ አትግቡ ብሎ አልላከህም፥


እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚህች ክፉ ወገን የተረፉ ቅሬታዎች ሁሉ፥ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ።


ኖን። የኃጢአቶቼ ቀንበር በእጁ ተይዛለች፥ ታስረው በአንገቴ ላይ ወጥተዋል፥ ጕልበቴን አደከመ። ጌታ በፊታቸው እቆም ዘንድ በማልችላቸው እጅ አሳልፎ ሰጠኝ።


ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፥ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውን ቃል ፈጸመ፥ አፈረሰ አልራራምም፥ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፥ የሚያስጨንቁሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ።


አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፥ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም።


አሁንም እኔ ናቡከደነፆር የሰማይን ንጉሥ አመሰግናለሁ፥ ታላቅም አደርገዋለሁ፥ አከብረውማለሁ። ሥራው ሁሉ እውነት፥ መንገዱም ፍርድ ነውና፥ በትዕቢትም የሚሄዱትን ያዋርድ ዘንድ ይችላልና።


ከርዋጪም ሽሽት ይጠፋል፥ ብርቱውም በብርታቱ አይበረታም፥ ኃያሉም ነፍሱን አያድንም፥ ቀስተኛውም አይቆምም፥


የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር በእናንተ፥ ከግብጽ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፥


እንዲህም ብሎአል፦ እኔ ከምድር ወገን ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፥ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።


ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል።


በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።


እነርሱም ስለ ነፍሴ ነፍሳቸውን ለሞት አቀረቡ፥ የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኑአቸው ናቸው እንጂ እኔ ብቻ አይደለሁም፤


ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።


በራብና በጥማት በዕራቁትነትም ሁሉንም በማጣት እግዚአብሔር ለሚልክብህ ለጠላቶችህ ትገዛለህ፤ እስኪያጠፋህም ድረስ በአንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭናል።


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


跟着我们:

广告


广告