Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፥ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፥ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤ የሰውን ቤት፣ የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የእርሻ ቦታዎችን ይመኛሉ፥ ይይዟቸዋልም፤ ቤቶችንም፥ ይወስዷቸዋልም፤ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ውርሱን ይጨቁናሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የእርሻ ቦታ ሲፈልጉ የሌላውን ቀምተው ይወስዳሉ፤ ቤትም ሲፈልጉ ነጥቀው ይወስዳሉ፤ የሰውን መብት ረግጠው ሀብቱን ይዘርፋሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፥ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፥ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።

参见章节 复制




ሚክያስ 2:2
28 交叉引用  

የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ጭፍራውን ሁሉ ሰበሰበ፤ ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገሥት ነበሩ፥ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበበ፥ ወጋትም።


‘በእውነት የናቡቴንና የልጆቹን ደም ትናንትና አይቻለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በዚህም እርሻ እመልስብሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል ወስደህ በእርሻው ውስጥ ጣለው።”


እርሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ እንደ ሆነ፥ ትልሞችዋም በአንድ ላይ አልቅሰው እንደ ሆነ፥


የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።


እግዚአብሔር ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከአለቆቻቸው ጋር ይፋረዳል፥ የወይኑን ቦታ የጨረሳችሁ እናንተ ናችሁ፥ ከድሆች የበዘበዛችሁት በቤታችሁ አለ፥


ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻን ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!


ዓይንህና ልብህ ግን ለስስት ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።


ድሀውንና ችግረኛውንም ቢያስጨንቅ ቢቀማም መያዣውንም ባይመልስ ዓይኖቹንም ወደ ጣዖታት ቢያነሣ ርኩስን ነገር ቢያደርግ፥


በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ከባልንጀሮችሽም በቅሚያ የስስትን ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ አንቺ ባደረግሽው ስስት በመካከልሽም በነበረው ደም ላይ እጄን አጨበጨብሁ።


ሰይፋችሁን ይዛችሁ ቆማችኋል፥ ርኩስ ነገርን ታደርጋላችሁ፥ የባልንጀሮቻችሁንም ሚስቶች ታስነውራላችሁ፥ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል አለቆች ሆይ፥ ይብቃችሁ፥ ግፍንና ብዝበዛን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ፥ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አርቁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


አለቃውም ሕዝቡን ከይዞታቸው ያወጣቸው ዘንድ ከርስታቸው በግድ አይውሰድ፥ ሕዝቤ ሁሉ ከይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆች ርስትን ይስጥ።


እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? በዚህ የሚያደርጉትን ይህን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ ለይሁዳ ቤት ጥቂት ነገር ነውን? ምድሪቱን በግፍ ሞልተዋታል ያስቈጡኝም ዘንድ ተመልሰዋል፥ እነሆም፥ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫው አቅርበዋል።


የድሆችን ራስ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፥ የትሑታንንም መንገድ ያጣምማሉ፥ ቅዱሱንም ስሜን ያረክሱ ዘንድ አባትና ልጁ ወደ አንዲት ሴት ይገባሉ፥


በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችጋረኞችንም የምታሰጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ።


ችጋረኛውን የምትውጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ እናንተ ሆይ፦


ፍርድን የምትጠሉ ቅን ነገርንም ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ።


ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፥ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፥ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።


跟着我们:

广告


广告