Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ያዕቆብ ሆይ፥ ሁልንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፥ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፥ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ያዕቆብ ሆይ፤ በርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልንም ትሩፍ በአንድነት አመጣለሁ፤ በጕረኖ ውስጥ እንዳሉ በጎች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ በአንድነት እሰበስባቸዋለሁ፤ ቦታውም በሕዝብ ይሞላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ያዕቆብ ሆይ፥ ሁላችሁንም ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልን ትሩፍ በአንድ ላይ እሰበስባለሁ፤ በጋጣ ውስጥ እንዳሉ በጎች፥ በማሰማርያው ውስጥ እንዳለ መንጋ አደርገዋለሁ፤ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “የእስራኤል ሕዝብ! በጎች በበረት፥ የበግ መንጋም በማሰማሪያ ቦታ እንደሚሰበሰብ በእርግጥ ከእስራኤል ሕዝብ የተረፉትን በአንድነት እሰበስባለሁ፤ ምድሪቱም በሕዝብ የተሞላች ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ያዕቆብ ሆይ፥ ሁልንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፥ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፥ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።

参见章节 复制




ሚክያስ 2:12
28 交叉引用  

ባላቅም ሞተ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ ኢዮባብም ሞተ


ባላቅም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ የባሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደገና እጁን ይገልጣል።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።


እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፥ በስብም፥ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ኵላሊት ስብ ወፍራለች።


የበግ ጠቦቶች በማሰማሪያቸው ውስጥ ይሰማራሉ፥ እንግዶችም የሰቡትን ባድማ ይበላሉ።


የመንጋዬም ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ፥ እነርሱም ያፈራሉ ይበዙማል።


በዚያም ዘመን የይሁዳ ቤት ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳል፥ በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ እፈልግማለሁ።


ከአሕዛብም ዘንድ አወጣቸዋለሁ ከአገሮችም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም አመጣቸዋለሁ፥ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በፈሳሾችም አጠገብ በምድርም ላይ ሰዎች በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።


ስለዚህ መንጋዬን አድናለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ንጥቂያ አይሆኑም፥ በበግና በበግ መካከልም እፈርዳለሁ።


እናንተም በጎቼ፥ የማሰማርያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ እኔም አምላካችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።


አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ከአሕዛብ መካከል እወስዳለሁ ከስፍራም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፥


በቴማን ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የባሶራንም አዳራሾች ትበላለች።


ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፥ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፥ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።


አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።


የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።


በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል።


በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።


በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፥ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告