Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 8:32 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ በውኃም ውስጥ ሞቱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ኢየሱስም፣ “ሂዱ!” አላቸው። አጋንንቱም ከሰዎቹ ወጥተው ዐሣማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ ዐሣማዎቹም በሙሉ ከነበሩበት አፋፍ እየተጣደፉ ባሕሩ ውስጥ በመግባት ውሃው ውስጥ ሰጥመው ሞቱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 እርሱም “ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ወጥተው ወደ አሣማዎቹ ሄደው ገቡ፤ እነሆ የዓሣማዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር ሮጡ፥ በውኆቹ ውስጥ ሰጥመው ሞቱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ኢየሱስም “ሂዱ!” አላቸው። ስለዚህም ከሰዎቹ ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ሄዱና ገቡባቸው። ዐሣማዎቹም በሙሉ ከገደሉ አፋፍ ላይ እየተንደረደሩ ወርደው በባሕር ውስጥ ሰጥመው ሞቱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ፤ በውሃም ውስጥ ሞቱ።

参见章节 复制




ማቴዎስ 8:32
10 交叉引用  

እግዚአብሔርም ‘በምን?’ አለው፤ እርሱም ‘ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ፤’ አለ። እግዚአብሔርም ‘ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፤ ይሆንልሃልም፤ ውጣ፤ እንዲሁም አድርግ፤’ አለ።


አጋንንቱም፦ ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን ብለው ለመኑት። ሂዱ አላቸው።


እረኞችም ሸሹ፥ ወደ ከተማይቱም ሄደው ነገሩን ሁሉ አጋንንትም በአደሩባቸው የሆነውን አወሩ።


ኢየሱስም ፈቀደላቸው። ርኵሳን መናፍስቱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ገቡ፥ ሁለት ሺህም የሚያህል መንጋ ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና በባሕር ሰጠሙ።


አጋንንትም ከሰውዬው ወጥተው ወደ እሪያዎች ገቡ፥ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና ሰጠሙ።


እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።


ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፥


跟着我们:

广告


广告