Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 8:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወዳለሁ፥ ንጻ አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ!” አለው። ሰውየውም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “ፈቅጃለሁ፤ ንጻ!” አለው። ለምጻሙም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።

参见章节 复制




ማቴዎስ 8:3
19 交叉引用  

እግዚአብሔርም፤ ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።


ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፤ እንዲህም አለ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር።


ወረደም፤ የእግዚአብሔርም ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፤ ንጹሕም ሆነ።


እርሱም፦ እጅህን ወደ ብብትህ መልስ አለው። እጁንም ወደ ብብቱ መለሳት፥ ከብብቱም ባወጣት ጊዜ እነሆ ተመልሳ ገላውን መሰለች።


ከዚያም በኋላ ሰውየውን፦ እጅህን ዘርጋ አለው። ዘረጋትም፥ እንደ ሁለተኛይቱም ደህና ሆነች።


ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወድዳለሁ፤ ንጻ አለው።


ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም፦ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።


የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ፦ ጣሊታ ቁሚ አላት፤ ፍችውም አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው።


ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና፦ ኤፍታህ አለው፥ እርሱም ተከፈት ማለት ነው።


ኢየሱስም ሕዝቡ እንደ ገና ሲራወጥ አይቶ ርኵሱን መንፈስ ገሠጸና፦ አንተ ዲዳ ደንቆሮም መንፈስ፥ እኔ አዝሃለሁ፥ ከእርሱ ውጣ እንግዲህም አትግባበት አለው።


በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፥ ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልነጻም።


እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወዳለሁ፥ ንጻ አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው።


ቀርቦም ቃሬዛውን ነካ፥ የተሸከሙትም ቆሙ፤ አለውም፦ አንተ ጐበዝ፥ እልሃለሁ፥ ተነሣ።


ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ “አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና” ብሎ ጮኸ።


ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደረግሁ፥ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል።


አብ ሙታንን ይንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።


跟着我们:

广告


广告