Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 26:69 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

69 ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ፦ አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

69 ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ሳለ አንዲት የቤት ሠራተኛ ወደ እርሱ ቀርባ፣ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋራ ነበርህ” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

69 ጴጥሮስም ከቤት ውጪ በግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድ ወደ እርሱ ቀርባ “አንተም ከገሊላዊው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ” አለችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

69 ጴጥሮስ ከቤት ውጪ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ በዚያን ጊዜ አንዲት ገረድ ወደ እርሱ ቀርባ “አንተም ከገሊላዊው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

69 ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ “አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ፤” አለችው።

参见章节 复制




ማቴዎስ 26:69
18 交叉引用  

ኤልያስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው ደጃፍ ቆመ። እነሆ “ኤልያስ ሆይ! በዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።


እዚያም ወዳለ ዋሻ መጣ፥ በዚያም አደረ። እነሆም “ኤልያስ ሆይ! በዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።


ሕዝቡም፦ ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው አሉ።


በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥


ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፥ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።


እርሱ ግን፦ የምትዪውን አላውቀውም ብሎ በሁሉ ፊት ካደ።


ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት፦ ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ አለች።


ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።


ሌሎች፦ “ይህ ክርስቶስ ነው” አሉ፤ ሌሎች ግን፦ “ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን?


እነርሱም መለሱና፦ “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ” አሉት።


ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ ተነሣ ብዙ ሰዎችንም አሸፍቶ አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ።


跟着我们:

广告


广告