Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሄሮድስ ጠቢባኑ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ በጣም ተናደደ። ከጠቢባኑ በተነገረው መሠረት፣ ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን የቤተ ልሔምንና የአካባቢዋን መንደሮች ወንድ ልጆች ሁሉ ልኮ አስገደለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፥ ወታደሮችን ልኮ ከሰብአ ሰገል በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን በቤተ ልሔምና በአካባቢዋ የነበሩትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚያ በኋላ ሄሮድስ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎቹ እንዳታለሉት በተገነዘበ ጊዜ፥ በጣም ተቈጣ፤ ወደ ቤተልሔምና በዙሪያዋም ወዳሉት መንደሮች ሁሉ ወታደሮቹን ልኮ፥ ከከዋክብት ተመራማሪዎቹ በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ዕድሜአቸው ሁለት ዓመት የሆናቸውንና ከዚያ በታች የሆኑትን በቤተልሔምና በአካባቢው የነበሩትን ወንዶች ሕፃናትን አስገደለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።

参见章节 复制




ማቴዎስ 2:16
21 交叉引用  

የቤትዋን ሰዎች ወደ እርስዋ ጠርታ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው፦ እዮ ዕብራዊው ሰው በእኛ እንዲሣለቅ አግብቶብናል፤ እርሱ ከእኔ ጋር ሊተኛ ወደ እኔ ገባ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ፤


ይህንም ነገር እንዲህ ብላ ነገረችው፦ ያገባህብን ዕብራዊው ባሪያ ሊሣለቅብኝ ወደ


ቍጣቸው ርጉም ይሁን ጽኑ ነበርና ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።


አዛሄልም “ጌታዬ ለምን ያነባል?” አለ። እርሱም “በእስራኤል ልጆች ላይ የምታደርገውን ክፋት ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ጕልማሶቻቸውንም በሰይፍ ትገድላለህ፤ ሕፃናቶቻቸውንም ትፈጠፍጣለህ፤ የእርጉዞቻቸውንም ሆድ ትቀድዳለህ፤” አለው።


እግዚአብሔርን የጠራሁ እርሱም የመለሰልኝ እኔ ለባልንጀራው መሳለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፥ ጻድቅና ፍጹም ሰው መሳለቂያ ሆኖአል።


በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቍጣውን ያመጣባቸው ዘንድ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፥ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፥ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።


እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፥ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፥ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው፥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።


ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፥ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው።


በሕዝብህም መካከል ሽብር ይነሣል፥ እናትም ከልጆችዋ ጋር በተፈጠፈጠች ጊዜ ሰልማን ቤትአርብኤልን በሰልፍ ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።


በለዓምም አህያይቱን፦ ስላላገጥሽብኝ ነው፤ በእጄስ ሰይፍ ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር አላት።


የባላቅም ቍጣ በበለዓም ላይ ነደደ፤ እጆቹንም አጨበጨበ፤ ባላቅም በለዓምን፦ ጠላቶቼን ትረግም ዘንድ ጠራሁህ፥ እነሆም፥ ሦስት ጊዜ ፈጽመህ መረቅሃቸው፤ አሁንም እንግዲህ ወደ ስፍራህ ሽሽ፤


ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።


ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥


ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።


ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።


ደሊላም ሶምሶንን፦ እነሆ፥ አታለልኸኝ፥ የነገርኸኝም ሀሰት ነው፥ አሁንም የምትታሰርበት ምን እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለችው።


跟着我们:

广告


广告