Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 8:23 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፥ በዓይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት፦ አንዳች ታያለህን ብሎ ጠየቀው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እርሱም የዐይነ ስውሩን እጅ ይዞ ከሰፈር ውጭ አወጣው፤ በዐይኖቹም ላይ እንትፍ ብሎበት፣ እጁንም በላዩ ጭኖ፣ “ምን የሚታይህ ነገር አለ?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እርሱም የዐይነ ስውሩን እጅ ይዞ ከሰፈር ውጭ አወጣው፤ በዐይኖቹም ላይ እንትፍ ብሎበት፥ እጁንም በላዩ ጭኖ፥ “ምን የሚታይህ ነገር አለ?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እርሱም ማየት የተሳነውን ሰው እጅ ይዞ እየመራ ከመንደር ወደ ውጪ አወጣው፤ በሰውየውም ዐይኖች ላይ ምራቁን እንትፍ ብሎ እጁን ጫነበትና “አንዳች ነገር ታያለህን?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፤ በዐይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት “አንዳች ታያለህን?” ብሎ ጠየቀው።

参见章节 复制




ማርቆስ 8:23
12 交叉引用  

የፈጠረህ ከማኅፀንም የሠራህ የሚረዳህም እግዚአብሔር እንዲህ ያልል፦ ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ይሹሩን ሆይ፥ አትፍራ።


ከወለደቻቸው ልጆች ሁሉ የሚመራት የለም፥ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም።


ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፥ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።


ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት ብሎ አጥብቆ ለመነው።


እጁንም ይጭንበት ዘንድ ለመኑት። ከሕዝቡም ለይቶ ለብቻው ወሰደው፥ ጣቶቹንም በጆሮቹ አገባ እንትፍም ብሎ መላሱን ዳሰሰ፤


አሻቅቦም፦ ሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ አለ።


ወደ ቤቱም ሰደደውና፦ ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው።


የሻለቃውም እጁን ይዞ ፈቀቅ አለና ለብቻው ሆኖ፦ የምታወራልኝ ነገር ምንድር ነው? ብሎ ጠየቀው።


ሳውልም ከምድር ተነሣ፥ አይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት።


ከግብፅ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው ይላል ጌታ።


ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።


跟着我们:

广告


广告