Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 5:23 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት ብሎ አጥብቆ ለመነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ትንሿ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናትና ድና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” በማለት አጥብቆ ለመነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 “ትንሿ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናትና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” በማለት አጥብቆ ለመነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ትንሽዋ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናት፤ እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር እባክህ መጥተህ እጅህን ጫንባት!” ሲል አጥብቆ ለመነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት፤” ብሎ አጥብቆ ለመነው።

参见章节 复制




ማርቆስ 5:23
26 交叉引用  

ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፤ እንዲህም አለ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር።


እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወዳለሁ፥ ንጻ አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።


የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።


ከእርሱም ጋር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም።


ብዙ ድውዮችንም ዘይት እየቀቡ ፈወሱአቸው።


ደንቆሮና ኰልታፋም የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፥


ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፥ በዓይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት፦ አንዳች ታያለህን ብሎ ጠየቀው።


ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።


በምኵራብም ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት በብርቱ ንዳድ ታማ ነበር ስለ እርስዋም ለመኑት።


ፀሐይም በገባ ጊዜ በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙ በሽተኞችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡአቸው፤ እርሱም በእያንዳቸው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው።


ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ የሞተ ሰው ተሸክመው አወጡ፤ እርሱም ለእናቱ አንድ ልጅ ነበረ፥ እርስዋም መበለት ነበረች፥ ብዙም የከተማ ሕዝብ ከእርስዋ ጋር አብረው ነበሩ።


ስለዚህ እኅቶቹ “ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል” ብለው ወደ እርሱ ላኩ።


የፑፕልዮስም አባት በንዳድና በተቅማጥ ታሞ ተኝቶ ነበር፤ ጳውሎስም ወደ እርሱ ገብቶ ጸለየለት እጁንም በላዩ ጭኖ ፈወሰው።


በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።


በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ።


እነሆ፥ እርሱ ይጸልያልና፤ ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቶአል” አለው።


ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ “ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ” አለ።


跟着我们:

广告


广告