Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 3:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም፦ ብዔል ዜቡል አለበት፤ ደግሞ፦ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ብለው ተናገሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከኢየሩሳሌም የመጡ ጸሐፍትም፣ “ብዔልዜቡል ዐድሮበታል! አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጸሐፍትም “በብዔልዜቡል ተይዟል! ደግሞም በዚህ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል!” ብለው ተናገሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከኢየሩሳሌም የወረዱ የሕግ መምህራን፥ “እርሱ ብዔልዜቡል አለበት! አጋንንትንም የሚያወጣው በዚሁ የአጋንንት አለቃ በሆነው በብዔልዜቡል አማካይነት ነው!” እያሉ አወሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም “ብዔል ዜቡል አለበት፤” ደግሞ “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” ብለው ተናገሩ።

参见章节 复制




ማርቆስ 3:22
14 交叉引用  

አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ ከዐይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም “ሂዱ፤ ከዚህም ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ፤” ብሎ መልእክተኞችን ላከ።


ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!


ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት።


ፈሪሳውያን ግን ሰምተው፦ ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ።


በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና፦


ፈሪሳውያን ግን፦ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ።


ፈሪሳውያንና ከጻፎች ወገን ከኢየሩሳሌም የመጡትም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።


ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዱ፦ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ።


አንድ ቀንም ያስተምር ነበር፤ ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮችም ሁሉ ከኢየሩሳሌምም መጥተው የነበሩ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ይቀመጡ ነበር፤ እርሱም እንዲፈውስ የጌታ ኃይል ሆነለት።


በኢየሩሳልውምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤


ሕዝቡ መለሱና፦ “ጋኔን አለብህ፤ ማን ሊገድልህ ይፈልጋል?” አሉት።


አይሁድ መልሰው፦ “ሳምራዊ እንደ ሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም እንል የለምን?” አሉት።


አይሁድ፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም ስንኳ ሞተ ነቢያትም አንተም፦ ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አይቀምስም’ ትላለህ።


跟着我们:

广告


广告