Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 14:65 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

65 አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና፦ ትንቢት ተናገር ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

65 በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ይተፉበት ጀመር፤ ዐይኑንም ሸፍነው በጡጫ እየመቱት፣ “ትንቢት ተናገር!” ይሉት ነበር። ጠባቂዎቹም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

65 በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ይተፉበት ጀመር፤ ዐይኑንም ሸፍነው በጡጫ እየመቱት፥ “እስቲ ትንቢት ተናገር” ይሉት ነበር። ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

65 አንዳንዶችም ምራቃቸውን እንትፍ ይሉበት ጀመር፤ ዐይኑንም በጨርቅ ሸፍነው “አንተ ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደ መታህ ዕወቅ!” እያሉ በቡጢ ይመቱት ነበር። ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

65 አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና “ትንቢት ተናገር፤” ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።

参见章节 复制




ማርቆስ 14:65
17 交叉引用  

የክንዓናም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፤ ሚክያስንም በጥፊ መታውና “የእግዚአብሔር መንፈስ ከአንተ ጋር ይናገር ዘንድ በምን መንገድ ከእኔ አለፈ?” አለ።


ንጉሡም ከቤቱ አታክልት ወደ ወይን ጠጁ ግብዣ ስፍራ ተመለሰ፥ ሐማም አስቴር ባለችበት አልጋ ላይ ወድቆ ነበር። ንጉሡም፦ ደግሞ በቤቴ በእኔ ፊት ንግሥቲቱን ይጋፋታልን? አለ። ይህም ቃል ከንጉሡ አፍ በወጣ ጊዜ የሐማን ፊት ሸፈኑት።


ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ራቁ፥ አክታቸውንም በፊቴ መትፋትን አልተዉም።


ጀርባዬን ለገራፊዎች ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠሁ፥ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።


ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፥


የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፥ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።


የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፥ ከብቦ አስጨንቆናል፥ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰፈር ውጭ ተዘግታ ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ አለው።


ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።


ይዘብቱበትማል ይተፉበትማል ይገርፉትማል ይገድሉትማል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው።


ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት።


ይህንም ሲል በዚያ ቆሞ የነበረው ከሎሌዎች አንዱ፦ “ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን?” ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው።


እየቀረቡም፦ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን” ይሉት ነበር፤


ሊቀ ካህናቱም ሐናንያ አፉን ይመቱት ዘንድ በአጠገቡ ቆመው የነበሩትን አዘዘ።


跟着我们:

广告


广告