Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 10:47 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ፦ የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በሰማ ጊዜ፣ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በሰማ ጊዜ፥ “የዳዊት ልጅ፥ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ” እያለ ይጮኽ ጀመር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 በዚያም የሚያልፈው የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን ባወቀ ጊዜ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ እባክህ ራራልኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ!” ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር።

参见章节 复制




ማርቆስ 10:47
24 交叉引用  

ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።


የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።


ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና፦ እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ።


እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች።


በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።


እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን ብለው ጮኹ።


ሕዝቡም፦ ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው አሉ።


የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።


ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት፦ ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ አለች።


ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች፦ የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረን ብለው እየጮሁ ተከተሉት።


እርሱም፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፥ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ ጮኸ።


ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ።


ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።


ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም፦ “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ነበረ።


ሌሎች፦ “ይህ ክርስቶስ ነው” አሉ፤ ሌሎች ግን፦ “ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን?


እነርሱም መለሱና፦ “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ” አሉት።


ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና” የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ።


እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።


跟着我们:

广告


广告