Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚልክያስ 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዔሳውን ግን ጠላሁ፤ ተራሮቹን ባድማ አደረግሁ፤ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮዎች ሰጠሁበት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዔሳውን ግን ጠላሁት፤ ተራራውን አጠፋሁ፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች ሰጠኋቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዔሳውን ግን ጠላሁ፤ የዔሳውን ኰረብታማ አገር ወደ ምድረ በዳ ለወጥኩ፤ ምድሩንም የቀበሮ መፈንጫ አደረግሁት።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።

参见章节 复制




ሚልክያስ 1:3
26 交叉引用  

እግዚአብሔርም አላት፦ ሁለት ወገኖች በማኅፀንሽ ናቸው ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።


ደረቂቱ ምድር ኵሬ፥ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፥ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸምበቆው ደንገልም ይሆንበታል።


እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የተሸሸጉትንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ ይሸሸግም ዘንድ አይችልም፥ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።


ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፥ በእውነት የመንጋ ትንንሾች ይጐተታሉ፥ በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል።


አሶርም የቀበሮ መኖሪያና የዘላለም ባድማ ትሆናለች፥ በዚያም ሰው አይኖርም፥ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም።


ስለ ኤዶምያስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን?


ጥበባቸውስ አልቆአልን? እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ፥ የዔሳውን ጥፋት፥ የምጐበኝበትን ጊዜ፥ አመጣበታለሁና ሽሹ፥ ወደ ኋላ ተመለሱ፥ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ።


ባቢሎንም የድንጋይ ቍልልና የቀበሮ ማደሪያ መደነቂያም ማፍዋጫም ትሆናለች፥ የሚቀመጥባትም ሰው አይገኝም።


ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይቀመጥባት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


ታው። የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የበደልሽ ቅጣት ተፈጸመ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም። የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ በደልሽን ይቀጣል፥ ኃጢአትሽን ይገልጣል።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ ስድባቸውን በእርግጥ ይሸከማሉ ብዬ ምያለሁ።


እነሆ፥ እኔ ለእናንተ ነኝና፥ ወደ እናንተም እመለከታለሁ፥ እናንተም ትታረሳላችሁ ይዘራባችሁማል፥


በአገራቸው ንጹሑን ደም አፍስሰዋልና በይሁዳ ልጆች ላይ ስላደረጉት ግፍ ግብጽ ምድረ በዳ፥ ኤዶምያስም በረሃ ይሆናል።


በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስለ ተደረገ ግፍ እፍረት ይከድንሃል፥ ለዘላለምም ትጠፋለህ።


ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።


跟着我们:

广告


广告